ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ታኅሣሥ እና ጥር:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። “መንግሥትህ ትምጣ” የተባለውን መጽሐፍም ማበርከት ይቻላል። የካቲት:- ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም ጉባኤው ያለውን ሌላ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል።
◼ ጉባኤዎች በታኅሣሥ ወር ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2002 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። መጽሐፉ የሚገኘው በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛና በጣልያንኛ ቋንቋዎች ነው። መጽሐፉ ደርሶን እስክንልክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የጽሑፍ መላኪያ ዝርዝር ላይ “በቅርቡ የሚደርስ” ተብሎ ይወጣል። የዓመት መጽሐፍ በልዩ ትእዛዝ የሚገኝ ጽሑፍ ነው።
◼ ጉባኤዎች በታኅሣሥ ወር ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2001 የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞችን ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ጥራዞቹ ደርሰውን እስክንልክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የጽሑፍ መላኪያ ዝርዝር ላይ “በቅርቡ የሚደርስ” ተብሎ ይወጣል። ጥራዞች በልዩ ትእዛዝ የሚገኙ ጽሑፎች ናቸው።
◼ ለ2002 የመታሰቢያው በዓል የሚያገለግል የመጋበዣ ወረቀት በቅርቡ ለጉባኤያችሁ ይላካል። የመታሰቢያው በዓል ሐሙስ መጋቢት 28, 2002 ይከበራል።
◼ የ2002 የዓመት ጥቅስ የሚከተለው ነው:- “ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ።”—ማቴ. 11:28
ነ◼ በአየር ለሚላኩ ዓመታዊ የመጽሔት ኮንትራቶች የወጣውን አዲስ የፖስታ አገልግሎት ዋጋ ልብ በሉ:- የአማርኛ ወይም የትግርኛ መጠበቂያ ግንብ ከኢጣሊያ:- 162 ብር፤ የአማርኛ ንቁ!:- 81 ብር፤ መጠበቂያ ግንብ ወይም ንቁ! (እንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ) ከእንግሊዝ:- 69 ብር፤ ከካናዳ:- 139 ብር፤ ከዩ ኤስ ኤ:- 151 ብር። ለእያንዳንዱ በአየር የሚላክ የመጽሔት ኮንትራት ይህ የገንዘብ መጠን መከፈል አለበት። በተጨማሪም ለመጽሔቱ የወጣውን ወጪ ለመሸፈን አስተዋጽኦ ማድረግ ይበረታታል። በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በስፓኒሽና በጣልያንኛ ቋንቋዎች በወር ሁለት ጊዜ የሚወጡ መጽሔቶችን የያዙ የቴፕ ክሮች ኮንትራት የመላኪያ ዋጋ 126.50 ብር ነው።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2002፤ አረብኛ:- የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2፤ እንግሊዝኛ:- ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ—ሃው ቱ አቴይን ኢት፤ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2002፤ የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2፤ ትግርኛ:- ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች።
◼ በድጋሚ የደረሱን:- አማርኛ:- ታላቁ ሰው፤ የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1፤ T-19፤ T-20፤ T-21፤ እንግሊዝኛ:- አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፤ ኮንኮርዳንስ፤ ሲዲ:- የመንግሥቱ ጣዕመ ዜማዎች ቁጥር 8, 9፤ የውዳሴ መዝሙሮች (8 ሲዲዎች)፤ የቪዲዮ ክሮች:- የአዲሱ ዓለም ኅብረተሰብ በእንቅስቃሴ ላይ፤ መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ታሪክና አስተማማኝ ትንቢት፤ መጽሐፍ ቅዱስ—በሕይወትህ ውስጥ ያለው ኃይል።