ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከመስከረም 3 እስከ ታኅሣሥ 24, 2001 በነበሩት ሳምንታት በተሰጡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ተዘግቶ የሚደረግ የጽሑፍ ክለሳ። በሌላ ወረቀት ተጠቅመህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቻልከውን ያህል ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ስጥ።
[ማሳሰቢያ:- በጽሑፍ ክለሳው ወቅት ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ማየት የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። በቅንፍ ውስጥ የተጠቀሱት ጽሑፎች በግልህ ምርምር እንድታደርግባቸው የቀረቡ ናቸው። የትኛው መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ በሚጠቀስበት ጊዜ አንቀጹ የተሰጠው በሁሉም ቦታ ላይ አይደለም።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. እምነት የአምላክ መንፈስ ፍሬ ስለሆነ እምነት የሌላቸው ሰዎች ይህንን መንፈስ ለማግኘት አይጥሩም፣ ቢጥሩም እንኳ ዓላማቸው የተሳሳተ ይሆናል፤ አሊያም መንፈሱ በሕይወታቸው ውስጥ እንዲሠራ አይፈቅዱም። (ሉቃስ 11:13፤ ገላ. 5:22) [rs ገጽ 130 አን. 1]
2. መዝሙር 58:4 (አ.መ.ት) እፉኝት በተፈጥሮው መስማት ስለማይችል ‘ጆሮው’ ምንም ጥቅም እንደሌለው በትክክል ይገልጻል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ባለማጣቀሻው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ገጽ 1583ን ተመልከት።]
3. መዝሙር 68:11 ላይ “ብዙ ሠራዊት” ተብለው የተጠቀሱት ሴቶች የእስራኤል ወንዶች ጠላት ብሔራትን ድል አድርገው በያዙ ጊዜ ከምርኮኝነት ያስለቀቋቸው በባርነት ይኖሩ የነበሩ ባዕዳን ሴቶች ናቸው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w86 10/15 ገጽ 30 አን. 6ን ተመልከት።]
4. የእያንዳንዱ ሰው ዕድሜና አሟሟት ገና ሲወለድ ወይም ከዚያ ቀደም ብሎ የተወሰነ ከሆነ ከአደገኛ ሁኔታዎች መራቅ ወይም ጤንነትን መንከባከብ እና አደጋ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ ሞትን ስለማያስቀር አስፈላጊ አይሆንም ነበር። [rs ገጽ 139 አን. 1]
መ 5. ጳውሎስ “ማንም ታናሽነትህን አይናቀው” በማለት ሲናገር ጢሞቴዎስ ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ ወይም በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኝ መሆኑን ያሳያል። (1 ጢሞ. 4:11, 12) [w99 9/15 ገጽ 29 አን. 1-3፤ ገጽ 31 አን. 2]
6. መዝሙር 110:1 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ‘ጌታዬ’ የሚለው ቃል ኢየሱስን ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w94 6/1 ገጽ 28 አን. 5ን ተመልከት።]
7. በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ይሖዋ የሚለው ስም 700 ያህል ጊዜ የሚገኝ ሲሆን “ያህ” የሚለው አጭር የስሙ አጠራር ደግሞ 43 ጊዜ ይገኛል። በመሆኑም በጥቅሉ ሲታይ በእያንዳንዱ መዝሙር ላይ መለኮታዊው ስም በአማካይ 5 ጊዜ ያህል ተጠቅሶ ይገኛል። [si ገጽ 104 አን. 23]
8. በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ኢየሱስ “አምላክ” አልፎ ተርፎም “ኃያል አምላክ” እንደሆነ ቢነገርም እንኳ አንድም ቦታ ሁሉን ቻይ ተብሎ አልተጠራም። (ዮሐ. 1:1፤ ኢሳ. 9:6፤ ዘፍ. 17:1) [rs ገጽ 150 አን. 7]
9. የምሳሌን መጽሐፍ ማጥናት የራሱን የሰሎሞንን ጥበብ ከማጥናት ተለይቶ አይታይም። [si ገጽ 106 አን. 1]
10. ምሳሌ 21:17 ላይ የሚገኘው ‘ተድላን ከመውደድ’ ስለ መራቅ የቀረበው የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ጨዋታ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዮች ጊዜ ስለሚያሳጣ ስህተት መሆኑን ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 10/1 ገጽ 27 አን. 7ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ላሉት ጥያቄዎች መልስ ስጥ:-
11. ኢየሱስ ለማርታ በለዘበ መንፈስ የሰጣት ተግሣጽ ምን ያመለክታል? (ሉቃስ 10:40, 41) [w99 9/1 ገጽ 30 አን. 7]
12. ይሖዋ መዝሙራዊውን የተቀበለው ወደ ምን ዓይነት “ክብር” ነው? (መዝ. 73:24) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w86 12/15 ገጽ 28 አን. 3ን ተመልከት።]
13. መዝሙር 84:1-3 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው መዝሙራዊው ላገኛቸው የአገልግሎት መብቶች ያለውን አመለካከት የገለጸው እንዴት ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 3/15 ገጽ 8 አን. 5-7ን ተመልከት።]
14. ራእይ 22:17 እና ሮሜ 2:4, 5 ይሖዋ ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ አስቀድሞ እንደማያውቅ ወይም እንደማይወስን የሚያሳዩት እንዴት ነው? [rs ገጽ 141 አን. 3-4]
15. በራእይ መጽሐፍ ላይ ተጠቅሶ እንደሚገኘው የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በሺው ዓመት የክርስቶስ ንግሥና ያምኑ የነበረ ቢሆንም ውሎ አድሮ ከሃዲ ክርስቲያኖች ይህን መለኮታዊ ትምህርት እንዳይቀበሉ ያደረጋቸው ምንድን ነው? [w99 12/1 ገጽ 6 አን. 3–ገጽ 7 አን. 5]
16. ክርስቲያኖች ለሌሎች ሰዎች ‘የሚሰጡት የግል ትኩረት’ ገደብ ሊኖረው የሚገባው ለምንድን ነው? (ፊልጵ. 2:4) [w99 12/1 ገጽ 29 አን. 1]
17. መዝሙር 128:3 ላይ በአንድ ሰው ማዕድ ዙሪያ “እንደ ወይራ ቡቃያ” ስለሆኑ ወንዶች ልጆች መጠቀሱ ምን ሐሳብ ያስተላልፋል? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w00 8/15 ገጽ 30 አን. 4ን ተመልከት።]
18. የአምላክ ሥራ ፍርሃት የሚያሳድር መሆኑን ማስተዋላችን እንዴት ሊነካን ይገባል? (መዝ 139:14) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w93 10/1 ገጽ 15 አን. 18ን ተመልከት።]
19. ምሳሌ 5:3, 4 የሥነ ምግባር ብልግና የሚያስከትለው መዘዝ “እንደ እሬት የመረረ” እና “ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍም የተሳለ” እንደሆነ አድርጎ የሚናገረው ለምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w00 7/15 ገጽ 29 አን. 3ን ተመልከት።]
20. ከምሳሌ 14:29 ጋር በሚስማማ መንገድ ማስተዋል፣ ትዕግሥት ማጣትና በቁጣ መገንፈል የሚያስከትሉትን መዘዝ እንድናስወግድ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 3/15 ገጽ 13 አን. 7-8ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል (ቃላት) ወይም ሐረግ ስጥ:-
21. እውነተኛ ነቢያት ___________________________________ ተናግረዋል እንዲሁም ________________________________ አሳውቀዋል። (ዘዳ. 18:18-20; 1 ዮሐ. 4:1-3) [rs ገጽ 133 አን. 2፤ ገጽ 134 አን. 2]
22. የምሳሌ መጽሐፍ ድርብ ዓላማ አለው፤ _________________________ መስጠትና _________________________ ማስተማር። (ምሳሌ 1:1-4) [w99 9/15 ገጽ 13 አን. 1]
23. ‘የልዑል መጠጊያ’ _________________________________ በሚመለከተው አከራካሪ ጉዳይ ከአምላክ ጎን የቆሙ ሰዎች _______________________________ የሚያገኙበት ቦታ ነው። _________________________ ሰዎች ግን ቦታው ‘ምሥጢር’ ወይም የማይታወቅ ነው። (መዝ. 91:1) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w86 12/15 ገጽ 29 አን. 6ን ተመልከት።]
24. ‘የይሖዋን ሥራዎች ሁሉ አለመርሳት’ በ103ኛው መዝሙር ላይ እንደተገለጸው “ሥራዎቹን” ማለትም ፍቅራዊ ደግነቱን ባንጸባረቀበት ድርጊት ላይ _________________________________________ ጋር ግንኙነት እንዳለው ግልጽ ነው። (መዝ. 103:2) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 5/15 ገጽ 21 አን. 5-6ን ተመልከት።]
25. ምሳሌ _______________________________________ ያለበት እና _____________________________________ የታቀደ ቁም ነገር ያዘለ አባባል ነው። [si ገጽ 107 አን. 6]
ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. ሳኦል ባደረሰበት በደል የተነሳ የሚናደድበት ምክንያት ቢኖረውም እንኳ ዳዊት መንፈሱን የተቆጣጠረው (ሳኦል ፍጹም ሰው አለመሆኑን ስለተገነዘበና የአምላክ አገልጋዮች ይቅር ባዮች መሆን ስላለባቸው፤ ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና በግልጽ በአእምሮው ስለያዘ፤ ፈራጅ መሆን ስህተት መሆኑን ስለሚያውቅ) ነው። (1 ሳሙ. 24:6, 15) [w99 8/15 ገጽ 8 አን. 7]
27. (ጥበብ፤ ተግሣጽ፤ ጽድቅ) እውቀትን፣ ማስተዋልን፣ ብልህነትንና የማሰብ ችሎታን ጨምሮ ብዙ ባሕርያትን አጣምሮ የያዘ ነው። (በጎነት፤ ማስተዋል፤ ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ) አንድን ነገር በጥልቀት የመመልከትና የነገሩን ምንነት ለማወቅ የተለያዩ ክፍሎቹ እርስ በርስ ያላቸውን ግንኙነትና አጠቃላዩን ይዘት በማወቅ መዋቅሩን የመረዳት ችሎታ ነው። (ምሳሌ 1:1-4) [w99 9/15 ገጽ 13 አን. 2]
28. ዮሴፍ የጲጥፋራ ሚስት ያቀረበችለትን ሥነ ምግባር የጎደለው ጥያቄ አልቀበልም ለማለት ጥንካሬ ያገኘው (ምንዝር መፈጸም የሚያወግዘውን የሙሴን ሕግ ስለሚያውቅ፤ ለባለቤቷ ከፍተኛ ሥልጣን ጥልቅ አክብሮት ስለነበረው፤ ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና ከፍ አድርጎ ስለተመለከተ) ነው። (ዘፍ. 39:7-9) [w99 10/1 ገጽ 29 አን. 3]
29. የመዝሙር 119 ጸሐፊ በእያንዳንዱ የመዝሙሩ ቁጥሮች ላይ እንደጠቀሰው (ለአምላክ ቃል ወይም ሕግ፤ ለሕይወት ስጦታ፣ መዳን ለማግኘት ላለው ተስፋ) ጥልቅ አድናቆት እንደነበረው ግልጽ ነው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 11/1 ገጽ 10 አን. 1፤ w87 3/15 ገጽ 24 አን. 2ን ተመልከት።]
30. ጳውሎስ ለ(ሮሜ፣ ገላትያ፣ ዕብራውያን) ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ የመጀመሪያ ሁለት ምዕራፎች ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን (የላቀ ደረጃ፣ ጥምቀት፣ ምድራዊ አገልግሎት) በተመለከተ ከመዝሙራት የተወሰዱ በርካታ ጥቅሶችን እናገኛለን። [si ገጽ 105 አን. 28]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
ምሳሌ 2:19፤ 14:15፤ 18:17፤ ሮሜ 10:17፤ ዕብ. 13:18
31. አንድ ሰው እምነት ለማግኘት በመጀመሪያ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል መረዳትና በጥንቃቄ መመርመር ይኖርበታል። [rs ገጽ 131 አን. 3]
32. ክርስቲያኖች ሐቀኝነት በጎደላቸው ወይም ሌሎች ሊያገኙ የሚገባቸውን ጥቅም በሚነፍጉ የንግድ እንቅስቃሴዎች መካፈል አይችሉም። [w99 9/15 ገጽ 10 አን. 2]
33. የፆታ ብልግና የሚፈጽሙ ሰዎች ተመልሰው ሊወጡ ወደማይችሉበት ደረጃ ይኸውም ወደ ሞት አፋፍ ሊደርሱ ይችላሉ። [w99 11/15 ገጽ 27 አን. 5-6]
34. ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ሰው ድርጊቱ የሚያስከትልበትን መዘዝ ያመዛዝናል እንጂ ሰፊ ተቀባይነት ስላገኘ ብቻ አንድን አዲስ ፋሽን በጭፍን አይከተልም። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ gE94 12/8 ገጽ 16 አን. 1ን ተመልከት።]
35. ምንም እንኳ የአንድ ሰው የመከራከሪያ ነጥብ አሳማኝና ትክክለኛ መስሎ ቢታይም መደምደሚያ ላይ ከመድረስ በፊት ሁለቱንም ወገኖች መስማቱ ጥበብ ነው። [si ገጽ 111 አን. 36]