መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት ላበረከትክላቸው ሰዎች ተመላልሶ መጠይቅ ስታደርግ እንዲህ ልትል ትችላለህ፦
“ባለፈው ስንገናኝ አንድ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ሰጥቼዎት ነበር። የመጽሔቱ ሙሉ ስም የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ እንደሚል ምናልባት ሳያስተውሉ አይቀሩም። ይህ ምን ዓይነት መንግሥት እንደሆነና ለእርስዎም ሆነ ለቤተሰብዎ ምን ትርጉም እንዳለው ባወያይዎት ደስ ይለኛል።” ከዚያም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር ትምህርት 6ን ግለጥና ግለሰቡ ያለው ጊዜ እስከፈቀደልህ ድረስ እያነበባችሁ ተወያዩበት።
“በቅርቡ መጥቼ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ሰጥቼዎት ነበር። እነዚህ መጽሔቶች ለመጽሐፍ ቅዱስና መጽሐፍ ቅዱስ ለያዛቸው የሥነ ምግባር መመሪያዎች ከፍ ያለ አክብሮት እንዲኖረን ያበረታታሉ። ሁሉም ሰው የአምላክን ቃል በሚገባ መረዳቱ አስፈላጊ ነው ብዬ ስለማስብ እንዲህ ለማድረግ የሚረዳዎ አንድ ጽሑፍ ላሳይዎት ተመልሼ መጥቻለሁ።” አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር ወይም እውቀት መጽሐፍ አስተዋውቀውና መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንዲጀምር ግብዣ አቅርብለት።
የቆዩ ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት ስታበረክት ይህን አቀራረብ መጠቀም ትችላለህ፦
“ጥራት ያለው ትምህርት የማግኘት አስፈላጊነት ከፍተኛ ትኩረት ሲሰጠው ቆይቷል። በእርስዎ አመለካከት አንድ ሰው አስደሳችና ስኬታማ የሆነ ሕይወት ለመኖር ምን ዓይነት ትምህርት መከታተል አለበት ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ምሳሌ 9:10, 11ን አንብብ።] ይህ መጽሐፍ [ለማበርከት የያዝከውን ጽሑፍ ርዕስ ተናገር] በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ሲሆን ወደ ዘላለም ሕይወት ሊመራ የሚችለው እውቀት ከየት እንደሚገኝ ያመለክታል።” ከመጽሐፉ ውስጥ ለዚህ ማስረጃ የሚሆን አንድ ምሳሌ አሳየውና ወስዶ እንዲያነበው አበረታታው።
ፍላጎት በመቀስቀስ ረገድ ውጤታማ ሆኖ ያገኘኸው መግቢያ ካለ በእሱ መጠቀምህን መቀጠል ትችላለህ! በወሩ ውስጥ ለሚበረከተው ጽሑፍ እንዲስማማ አድርገህ አቅርበው።
[ገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ሌሎች ጽሑፎች
ሌሎች መጽሐፎችንና ብሮሹሮችን ለማበርከት የሚረዱ አቀራረቦችን የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ ላይ ቀጥሎ ባለው ዋና ርዕስ ሥር ማግኘት ይቻላል:-
አቀራረቦች (Presentations)
በጽሑፉ ዓይነት (List by publication)
[ገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ቀጥተኛ አቀራረብ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ቀጥሎ ከቀረቡት ቀጥተኛ አቀራረቦች መካከል አንዱን ለመጠቀም ሞክር:-
“ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ መሥዋዕት በማድረግ አስፈላጊ ለሆነ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ መልስ ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ? ለምሳሌ ያህል . . .” ከዚያም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር ውስጥ ካሉት ትምህርቶች በአንደኛው መግቢያ ላይ ከሰፈሩት ጥያቄዎች መካከል ለግለሰቡ ተስማሚ ነው ብለህ የምታስበውን አንዱን ጥያቄ ጠይቅ።
“የመጣሁት በነፃ የምንሰጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም ምን እንደሚመስል ላሳይዎት ነው። ጥናቱ እንዴት እንደሚካሄድ ለማሳየት አምስት ደቂቃ በቂ ነው። አምስት ደቂቃ ይኖርዎታል?” አዎ፣ የሚል መልስ ካገኘህ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር ትምህርት 1ን ተጠቅመህ ጥናቱ እንዴት እንደሚካሄድ አሳየው፤ እንዲሁም አንድ ወይም ሁለት ጥቅሶችን መርጠህ አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ “15 ደቂቃ ያህል ወስደን ቀጣዩን ትምህርት ለማጥናት መቼ ይመችዎታል?”
“ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው ቢሆንም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ሰዎች ለሚያነሷቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ እንደያዘ አይገነዘቡም። መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዳውን ይህን ጽሑፍ [አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት መጽሐፍ] በመጠቀም በየሳምንቱ ለአንድ ሰዓት ወይም ከዚያ ብዙም ለማይበልጥ ጊዜ ቢያጠኑ በጥቂት ወራት ውስጥ መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀቶች ሊጨብጡ ይችላሉ። የጥናት ፕሮግራሙ እንዴት እንደሚካሄድ ባሳይዎት ደስ ይለኛል።”
“የመጣሁት ቤትዎ ሆነው መጽሐፍ ቅዱስን በነጻ እንዲማሩ ግብዣ ላቀርብልዎት ነው። ከ200 በላይ በሚሆኑ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች በየቤታቸው መጽሐፍ ቅዱስን ከቤተሰባቸው ጋር እንዴት እንደሚያጠኑ ለጥቂት ደቂቃዎች ባሳይዎት ደስ ይለኛል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከቀረቡት ርዕሶች መካከል የፈለግነውን መርጠን ልንወያይበት እንችላለን። [እውቀት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን የአርዕስት ማውጫ አሳየው።] ከእነዚህ ርዕሶች መካከል በተለይ ለማወቅ የሚፈልጉት ስለየትኛው ነው?” ሰውየው እስኪመርጥ ድረስ ጠብቅ። የመረጠውን ምዕራፍ አውጣና በመጀመሪያው አንቀጽ ጥናቱን ጀምር።
“መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ ለሰዎች አስተምራለሁ፤ ተጨማሪ ተማሪዎችን ለማስጠናት የሚያስችል ጊዜ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት የምንጠቀመው በዚህ መጽሐፍ ነው። [እውቀት መጽሐፍ አሳየው።] ትምህርቱ ጥቂት ወራት ብቻ የሚፈጅ ሲሆን እንደሚከተሉት ላሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፦ አምላክ ሥቃይና መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው? በሞት የተለዩን የምንወዳቸው ሰዎች ምን ይሆናሉ? ከአምላክ ጋር መቀራረብ የምንችለው እንዴት ነው? ትምህርቱ እንዴት እንደሚካሄድ ላሳይዎት?”