ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። “መንግሥትህ ትምጣ” የተባለው መጽሐፍም ሊበረከት ይችላል። የካቲት፦ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም ጉባኤው ያለውን ማንኛውንም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። ሕይወት—እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍም ማበርከት ይቻላል። መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራው እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠይቅ በሚደረግበት ጊዜ ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ ኮንትራት እንዲገባ ግብዣ ማቅረብ ይቻላል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ።
◼ ጥር 14 የሚጀምር ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚገኙት የተጠመቁ አስፋፊዎች ሁሉ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ሰነድ ይሰጣቸዋል። ለልጆቻቸው ደግሞ የመታወቂያ ካርዱ ይሰጣል።
◼ ከመጋቢት 3 ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “አደጋ በሞላበት ዓለም ውስጥ ተረጋግቶ መኖር” የሚል ይሆናል።
◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2002 ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 14 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ “‘አስፈሪውን ቀን’ በአእምሯችሁ አቅርባችሁ ተመልከቱ” የሚል ነው። የንግግሩ አስተዋፅኦ ይላክላችኋል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። ማንኛውም ጉባኤ ከሚያዝያ 14, 2002 በፊት ልዩ የሕዝብ ንግግሩን ማቅረብ አይኖርበትም።
◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ሐሙስ መጋቢት 28 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ (ከ12 ሰዓት በኋላ) መጀመር ቢቻልም ምሳሌያዊው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቅበትን ሰዓት በአቅራቢያችሁ ከሚገኙ ምንጮች ጠይቃችሁ ተረዱ። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን ቢያከብር ይመረጣል። ባለፈው ዓመት በዓሉን ብቻቸውን ባከበሩ ጉባኤዎች የሚገኙ አስፋፊዎች ብዙ መልካም አስተያየቶች ሰንዝረዋል። ወንድሞች ተጋብዘው የመጡ ፍላጎት ያላቸው ሰዎችን በቀላሉ መለየትና ከሁሉም ተሰብሳቢዎች ጋር ሰላምታ መለዋወጥ በመቻላቸው ተደስተዋል። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን ለማድረግ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ ከሆነ ምናልባት አንዱ ወይም ሁለቱ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ መፈለግ ይችሉ ይሆናል። በአንድ አዳራሽ በየተራ የምትሰበሰቡ ከሆነ ከእንግዶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥና አዳዲሶችን ለማበረታታት የሚያስችል ጊዜ በመስጠት ሁሉም ከበዓሉ ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ በተቻለ መጠን በመካከል ቢያንስ የ30 ደቂቃ ልዩነት እንዲኖር እንድታደርጉ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። ተሳፋሪዎችን ማውረድንም ሆነ ማሳፈርን ጨምሮ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና የመኪና ማቆሚያ ቦታ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።
◼ ጥናት የሚያካሂዱ ሰዎችና ሌሎችም ስለ ይሖዋ ምሥክሮችና ስለ ድርጅታችን መረጃዎችን ለማግኘት አንዳንድ ወንድሞችን አነጋግረዋል። ከምናምንባቸውና ከምናስተምራቸው ነገሮች ጋር ግንኙነት ላላቸው ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥባቸው መጠይቆች እንዲሞሉላቸው ይጠይቃሉ። አንድ የጉባኤ አስፋፊ ይህን ዓይነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ወደ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ሊመራቸው ይችላል። ሽማግሌዎች ከቅርንጫፍ ቢሮ ጋር በመገናኘት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጡ ይችላሉ።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወርሃዊ ስቴትመንት ሲደርሰው ጉባኤው ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታና ለዓለም አቀፉ ሥራ ላደረጋቸው መዋጮዎች ማኅበሩ የላካቸው ምስጋናዎች በሙሉ ከሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ጋር እንዲነበቡ ማድረግ አለበት።