ለሠርግ ወራት የሚሆኑ ማሳሰቢያዎች
ክርስቲያናዊ ሠርጎች ለይሖዋ ክብር የሚያመጡና ዘመኑን እንድንዋጅ የሚያስችሉን እንዲሆኑ ለማድረግ ልናስተውላቸው የሚገቡ ነጥቦችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በወጡ ጽሑፎች ላይ ብዙ ጠቃሚ ምክር ተሰጥቷል። የሚከተሉትን ነጥቦች ታስታውሳቸዋለህ? ከሚያዝያ 15, 1997 ገጽ 23-26፤ ሚያዝያ 15, 1984 ገጽ 10-22 (እንግሊዝኛ) እና ግንቦት 1, 2000 ገጽ 19-22 መጠበቂያ ግንብ እትሞች የተወሰዱ ናቸው።
• የጋብቻ ሥነ ሥርዓቱ የግድ በተለመዱት የሠርግ ወራት መፈጸም ይኖርበታልን?
• የሠርግ ሥነ ሥርዓቱ የሚመለከታቸው ሁሉ ሌሎች ተጋባዦችን ያላግባብ ለረጅም ሰዓት ላለማስጠበቅ ሰዓት ያከብራሉ?
• ተጋባዦቹ በጋብቻ ንግግሩ ላይ ጭምር እንዲገኙ ተጋብዘዋል? ወይስ ጥሪ የቀረበላቸው በድግሱ ላይ እንዲገኙ ብቻ ነው?
• ለድግሱ የተጠሩት በአብዛኛው መንፈሳዊ ወንድሞችና እህቶች ናቸው?
• ፎቶግራፍ አንሺዎቹ ለሥነ ሥርዓቱ የሚስማማ ተገቢ ልብስ እንዲለብሱና ተናጋሪውን ወይም አድማጮችን እንዳይረብሹ ተነግሯቸዋል?
• የሠርጉ ፕሮግራም ከጉባኤ እንቅስቃሴዎች ጋር እንደማይጋጭ ታስቦበታልን?
• በድግሱ ላይ የተወገዱ ግለሰቦች ተገኝተው ሌሎች ተጋባዦች እንዳይሸማቀቁ ሲባል በቅድሚያ ምን የተደረገ ነገር አለ?
• ስለ ልከኝነት የሚገልጹ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክሮችንና ዝግጅቱ የተንዛዛ እንዳይሆን የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎችን ታስታውሳላችሁ?
• ሙዚቃ የሚኖር ከሆነ ተገቢ የሆኑ የሙዚቃ ዓይነቶች ተመርጠዋል? የሙዚቃው ድምፅ ተጋባዦቹ እርስ በእርስ የሚያደርጉትን ጭውውት የማይረብሽ ነው?
• አልኮል የሚቀርብ ከሆነ ቁጥጥር ይደረግበታል? የሚቀርበውስ በልክ ነው?
• ጭፈራ የሚኖር ከሆነ በማያስነቅፍ መንገድ ይደረጋል?
• ድግሱ የሚያበቃበት ሰዓት ሚዛናዊ ገደብ አለውን? ኃላፊነት የተሰጠው ግለሰብ እሰከዚህ ሰዓት ድረስ ይቆያል?
• የምናውቃቸው ዓለማዊ ሰዎች ሠርግ ላይ እንድንገኝ ስንጋበዝ በኤፌሶን 5:15, 16፣ በ1 ቆሮንቶስ 15:33 እንዲሁም በፊልጵስዩስ 1:10 ላይ እንደተጠቀሱት ያሉትን መሠረታዊ ሥርዓቶች እናስታውሳለን?