ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ቢገኙም ወደ ጉባኤ ስብሰባዎች አዘውትረው ለማይመጡ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍንና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። ሰኔ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር። ብሮሹሩን ስታበረክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሐምሌ እና ነሐሴ:- ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና የምትወዱት ሰው ሲሞት።
◼ ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መቅረብ አለበት።
◼ በ2004 ለሚደረጉት የአውራጃ ስብሰባዎች የወጣ ጊዜያዊ ፕሮግራም:-
መስ. 10-12አዲስ አበባእንግሊዝኛ
መስ. 17-19 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ3, 1ሐ, 7ለአማርኛ/የምልክት ቋንቋ
መስ. 24-26 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ1ሀ, 6ሀአማርኛ
ጥቅ. 1-3 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ5ሀ, 7ሀአማርኛ
ጥቅ. 8-10 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ2ሀ, 6ለአማርኛ
ጥቅ. 15-17 ወረዳ ቁ.አዲስ አበባ5ለአማርኛ
ጥቅ. 1-3ድሬዳዋአማርኛ
ጥቅ. 1-3ደሴአማርኛ
ጥቅ. 8-10ጅማአማርኛ
ጥቅ. 8-10መቀሌትግርኛ
ጥቅ. 15-17ሻሸመኔአማርኛ
ጥቅ. 15-17ነቀምትአማርኛ
ጥቅ. 15-17ባሕር ዳርአማርኛ
ጥቅ. 22-24ጊምቢኦሮምኛ
ጥቅ. 22-24ሶዶአማርኛ
ጥቅ. 22-24አለታ ወንዶአማርኛ
ጥቅ. 29-31ሶዶወላይትኛ
ጥቅ. 29-31አምቦኦሮምኛ
ጥቅ. 29-31ይርጋለምሲዳምኛ
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፦ የኢሳይያስ ትንቢት—2፤ እንግሊዝኛ፦ የ2004 የዓመት መጽሐፍ፤ ትግርኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፦ የመዝሙር መጽሐፍ፤ እንግሊዝኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ።