የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ግንቦት 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 86 (193)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ ካሉት አቀራረቦች ውስጥ ለጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል ተስማሚ የሆኑትን ተጠቅመህ የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2004 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሌሎች አቀራረቦችንም መጠቀም ትችላለህ። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ውይይቱን ለማስቆም “የራሴ ሃይማኖት አለኝ” ለሚል ሰው መልስ መስጠት የሚቻልባቸውን የተለያዩ መንገዶች የሚያሳዩ ይሁኑ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 18-19 ተመልከት።
15 ደቂቃ:- አንድነታችንን መጠበቅ። አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 153-157 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ዝቅ ተደርገው ለሚታዩ ሥራዎች፣ ላልተማሩ ወይም ድሃ ለሆኑ ሰዎችና ለተለያዩ ጎሳዎች ባለን አመለካከት ረገድ ምን ዓይነት ማስተካከያዎች ማድረግ እንደሚኖርብን ጎላ አድርገህ ግለጽ።
20 ደቂቃ:- “ፍቅራችሁን አስፉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የአምልኮ አንድነት ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 138 አንቀጽ 17 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “አመስጋኝ መሆናችሁን አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደ መጠን አድማጮች በጥቅሶቹ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ በቅርቡ ረዳት አቅኚ ሆነው ያገለገሉ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ረዳት አቅኚ መሆናቸው ያስገኘላቸውን በረከት እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- እርስ በርስ እንተሳሰባለን። (1 ቆሮ. 12:25, 26) አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 157-159 ላይ ባለው “እርስ በርስ መተሳሰብ” የሚል ንዑስ ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የይሖዋ ሕዝቦች በሁሉም የዓለም ክፍሎች የምንገኝ ቢሆንም የጠበቀ አንድነት አለን። ሁላችንም በየዕለቱ ለወንድሞቻችን መጸለይ ይኖርብናል። እንዲሁም አስቸኳይ እርዳታ በሚያስፈልግበት ወቅት በአፋጣኝ ቁሳዊ ድጋፍ መስጠት ይኖርብናል። ነጥቡን የሚደግፉ ቁልፍ ጥቅሶችን አንብብና ተወያዩባቸው፤ እንዲሁም ከጽሑፎቻችን ላይ አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 12 (32)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። የመጋቢት 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔትን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያው አብዛኛው የአካባቢው ኅብረተሰብ የሚከተለው ሃይማኖት አባል የሆነን ሰው ትኩረት በሚስብ መንገድ ይቅረብ።
15 ደቂቃ:- “መንፈስን የሚያድስ ሙዚቃ።” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከ2002 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 175 ላይ እና ከየካቲት 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 27 አንቀጽ 1-2 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
18 ደቂቃ:- ከቤት ወደ ቤትና መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር የተዘጋጃችሁ ሁኑ። በግንቦት 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 እና 9 ላይ እንዲሁም በሰኔ 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 ላይ ባለው ሐሳብ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከቤት ወደ ቤት በማገልገል ያገኟቸውን ተሞክሮዎች የሚናገሩ ጥቂት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክትና ጉድ ኒውስ ፎር ኦል ኔሽንስ የተባለውን ቡክሌት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነቱን ስንሰጥ እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 93 (211) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 9 (26)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
17 ደቂቃ:- ሕይወት—በእንክብካቤ መያዝ የሚገባው ስጦታ። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 25-26 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በጥር-መጋቢት 1994 ንቁ! መጽሔት ገጽ 10ና 11 ላይ ያለውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ። አንዲት ሴት ከራሷ አካል ጋር በተያያዘ ማንኛውንም ውሳኔ የማድረግ መብት አላት ብሎ ለሚያምን ሰው ይሖዋ ስለ ውርጃ ያለውን አመለካከት ምን ብለህ ታስረዳዋለህ? በጥር 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 4, አንቀጽ 4-5 ላይ የሚገኘውን ተሞክሮ ተናገር።
20 ደቂቃ:- “ለሰብዓዊ ባለ ሥልጣናት ሊኖረን የሚገባው አመለካከት።” እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት—እንዴት ማግኘት ትችላለህ? (እንግሊዝኛ) በተባለው መጽሐፍ ገጽ 134-136 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከአንቀጽ 13-15 ላይ በማተኮር በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ተወያዩ:- ሐቀኞችና ለሥልጣን አክብሮት ያለን መሆናችን ከመጻሕፍት፣ ከሙዚቃ ቅጂዎች ወይም ከኮምፒውተር ፕሮግራሞች ጋር በተያያዘ ለባለቤትነት መብት ያለንን አመለካከት የሚነካው እንዴት ነው? አንድ ክርስቲያን የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን አባዝቶ ለጓደኞቹ ከመስጠቱ በፊት ማረጋገጥ ያለበት ምን ነገር አለ? ሌሎች የትራፊክ ምልክቶችንና ሕጎችን ባያከብሩም እንኳ እኛ ማክበር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የትራፊክ ሕጎች ለእግረኞችና በብስክሌት ለሚንቀሳቀሱ ሰዎችም ይሠራሉ? መኪና ያለው ሰው የመኪናውን ደኅንነት በሚመለከት የትኞቹን ሕጎች ማስታወስ አለበት? የራሱን ንግድ የሚያንቀሳቅስ ሰው የትኞቹን ሕጎች ማክበር ይኖርበታል? አጥር ስናጥር ወይም በቤታችን ላይ ቀጥለን ስንሠራ የትኞቹን ሕጎች ማክበር ይኖርብናል? ባለ ሥልጣናት አንድ ነገር እንዲያከናውኑልን በምንጠይቅበት ወቅት ምንም ዓይነት እጅ መንሻ መስጠት የሌለብን ለምንድን ነው? (ምሳሌ 17:23) እጅ መንሻ መስጠት ለተደረገልን ሥራ መጠነኛ ስጦታ ከመስጠት የሚለየው እንዴት ነው?—ቆላ. 3:15
መዝሙር 14 (34) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ሰዎችን ለመርዳት የተደረገ ዝግጅት” ከሚለው ርዕስ ዋና ዋና ነጥቦችን አቅርብ። በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ከሚናገሯቸው የተለያዩ ቋንቋዎች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- በማስተማር ሥራችሁ ውጤታማ የሆኑ ምሳሌዎችን ተጠቀሙ። በመስከረም 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-24 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አንድን ምሳሌ ጥሩ የሚያሰኙት የትኞቹ አራት ነጥቦች ናቸው? ቀላል የሆኑ ምሳሌዎችን መጠቀሙ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው? ተስማሚ ምሳሌዎችን ከየት ልናገኝ እንችላለን? በገጽ 23 ላይ በሚገኘው ሣጥን ውስጥ ከቀረቡት ምሳሌዎች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስና ውጤታማ ሊሆኑ የቻሉበትን ምክንያት ተናገር።
መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።