-
በዘመናችን መቶ ዓመት ባስቆጠረው ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እየተካፈላችሁ ነውን?የመንግሥት አገልግሎት—2003 | ግንቦት
-
-
በዘመናችን መቶ ዓመት ባስቆጠረው ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እየተካፈላችሁ ነውን?
1 የይሖዋ ሕዝቦች በዘመናችን በተደራጀ መልኩ ከቤት ወደ ቤት ማገልገል ከጀመሩ በዚህ ወር መቶ ዓመት እንደሚሞላቸው ታውቃለህ? ምንም እንኳን ወንድሞች ከዚያ ቀደም ብለውም በግለሰብ ደረጃ ከቤት ወደ ቤት ያገለግሉ የነበረ ቢሆንም እያንዳንዱን ሰው ማግኘት እንዲቻል ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ትራክት እንዲያሰራጩ ማበረታቻ የተሰጠው በግንቦት 15, 1903 መጠበቂያ ግንብ ላይ ነበር። ኢየሱስና ሐዋርያቱ የተጠቀሙበት ይህ የስብከት ዘዴ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይበልጥ ስፋትና ጥራት ባለው መንገድ እየተሠራበት ነው። በተለይም በደንብ የታሰበበት ጥቅስ በመጠቀም ሰዎችን ለማነጋገር ጥረት ይደረጋል። (ማቴ. 10:12፤ ሥራ 5:42) ላለፉት በርካታ ዓመታት ከቤት ወደ ቤት የሚደረገው አገልገሎት የይሖዋ ምሥክሮች “መለያ ምልክት” ሆኖ ቆይቷል።
2 በአብዛኞቹ አገሮች ቀናተኛ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች የአገልግሎት ክልላቸውን በሙሉ በዓመት ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜያት፣ አንዳንድ ጊዜም በየወሩ ይሸፍናሉ። ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች ብዙ ሰዎች እምብዛም ቤታቸው አይገኙም። ስለሆነም ወንድሞች በመንገድ ላይ፣ በመናፈሻ ቦታዎች፣ በንግድ አካባቢዎች እንዲሁም ሰዎችን ማግኘት በሚቻልበት በማንኛውም ቦታና ጊዜ ሁሉ እንዲሰብኩ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል። በእኛ አገር ሰዎች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ መደበኛ በሆነና መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመስበክ ረዘም ላሉ ዓመታት ጥረት ሲደረግ የቆየ ሲሆን ይህም ጥሩ ውጤት አስገኝቷል። ይሁን እንጂ ለማንም ሳናዳላ ሁሉንም ሰው ማነጋገር እንድንችል ከቤት ወደ ቤት ሄደን ክልላችንን በመሸፈን ረገድ ብዙ መሥራት
-
-
ወንጌሉ በአደራ ተሰጥቶናልየመንግሥት አገልግሎት—2003 | ግንቦት
-
-
ወንጌሉ በአደራ ተሰጥቶናል
1 ስለ አምላክ የሚናገረውን ምሥራች የመስበክ አደራ የተሰጠን በመሆናችን ምንኛ ታድለናል! (1 ተሰ. 2:4) አንዳንዶች ይህንን መልእክት ለመቀበል ፈቃደኞች ባይሆኑም ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቱ ይስባቸዋል። (2 ቆሮ. 2:14-16) ወንጌሉን ለሚቀበሉና ለሚታዘዙ ሰዎች መዳን ያስገኛል። (ሮሜ 1:16) የተሰጠንን አደራ መወጣት የሚኖርብን እንዴት ነው?
2 ኢየሱስና ሐዋርያቱ:- ኢየሱስ ለወንጌሉ ስብከት ሥራ ቅድሚያ ይሰጥ ነበር። (ሉቃስ 4:18, 43) ለሰዎች ያለው ፍቅርና ለመልእክቱ ያለው አድናቆት ደክሞትና ርቦት በነበረበት ወቅት እንኳን እንዲሰብክ ገፋፍቶታል። (ማር. 6:30-34) ስለ አምላክ መንግሥት የመስበኩን አስፈላጊነት በቃልም ሆነ በድርጊት በደቀ መዛሙርቱ አእምሮ ውስጥ ቀርጿል።—ማቴ. 28:18-20፤ ማር. 13:10
3 ሐዋርያቱም የኢየሱስን ምሳሌ በመኮረጅ የመንግሥቱን መልእክት በትጋት አውጀዋል። ከተደበደቡና መስበካቸውን እንዲያቆሙ ከታዘዙም በኋላ እንኳን ‘ወንጌሉን ማስተማርንና መስበክን አልተዉም ነበር።’ (ሥራ 5:40-42) ሐዋርያው ጳውሎስም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በዚህ ሥራ ተካፍሏል። (1 ቆሮ. 15:9, 10፤ ቆላ. 1:29) ወንጌሉን የመስበክ ዕዳ እንዳለበት የተሰማው ሲሆን ይህንንም ለመፈጸም ሲል የግል ምቾቱን ለመተው ፈቃደኛ ነበር።—ሥራ 20:24፤ ሮሜ 1:14-16
4 ወንጌሉን የመስበክ መብታችን:- በአደራ ለተሰጠን ቅዱስ ተልዕኮ ያለን አድናቆት በስብከቱ ሥራ የምናደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉንን አጋጣሚዎች እንድንፈልግ ያነሳሳናል። (ሮሜ 15:15, 16) ያለ ተሽከርካሪ ወንበር መንቀሳቀስ የማይችለው ኤድዋርድ በአንድ ሆቴል ደጃፍ ላይ ተቀምጦ በሆቴሉ ላረፉት ሰዎች ስለ እምነቱ ይነግራቸው ነበር። ሆኖም ይበልጥ ማገልገል ስለፈለገ ለእርሱ የሚመቸው ለየት ያለ መኪና አሠርቶ በሺህ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በመጓዝ ለበርካታ ዓመታት በአቅኚነት አገልግሏል። እንደ ኤድዋርድ ሁሉ ዛሬም ብዙዎች ወንጌሉን ለሌሎች በማሰራጨቱ ሥራ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ ሲሉ አንዳንድ ማስተካከያዎችን አድርገዋል።
5 እንደ ኢየሱስና ሐዋርያቱ እኛም ለስብከቱ ሥራ ሁልጊዜ ቅድሚያ እንስጥ። እንዲህ ካደረግን ሰዎችን እንደምንወድና በአደራ ለተሰጠን ወንጌል አድናቆት እንዳለን እናሳያለን።
-