የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/03 ገጽ 1
  • ወንጌሉ በአደራ ተሰጥቶናል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወንጌሉ በአደራ ተሰጥቶናል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘መልካም ዜና ማብሰር’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ቅድሚያ የምትሰጡት ለምን ነገሮች ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ሁሉም ሰው የሚያስፈልገው ምሥራች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 5/03 ገጽ 1

ወንጌሉ በአደራ ተሰጥቶናል

1 ስለ አምላክ የሚናገረውን ምሥራች የመስበክ አደራ የተሰጠን በመሆናችን ምንኛ ታድለናል! (1 ተ⁠ሰ. 2:4) አንዳንዶች ይህንን መልእክት ለመቀበል ፈቃደኞች ባይሆኑም ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቱ ይስባቸዋል። (2 ቆ⁠ሮ. 2:14-16) ወንጌሉን ለሚቀበሉና ለሚታዘዙ ሰዎች መዳን ያስገኛል። (ሮሜ 1:16) የተሰጠንን አደራ መወጣት የሚኖርብን እንዴት ነው?

2 ኢየሱስና ሐዋርያቱ:- ኢየሱስ ለወንጌሉ ስብከት ሥራ ቅድሚያ ይሰጥ ነበር። (ሉቃስ 4:18, 43) ለሰዎች ያለው ፍቅርና ለመልእክቱ ያለው አድናቆት ደክሞትና ርቦት በነበረበት ወቅት እንኳን እንዲሰብክ ገፋፍቶታል። (ማር. 6:30-34) ስለ አምላክ መንግሥት የመስበኩን አስፈላጊነት በቃልም ሆነ በድርጊት በደቀ መዛሙርቱ አእምሮ ውስጥ ቀርጿል።​—⁠ማቴ. 28:18-20፤ ማር. 13:10

3 ሐዋርያቱም የኢየሱስን ምሳሌ በመኮረጅ የመንግሥቱን መልእክት በትጋት አውጀዋል። ከተደበደቡና መስበካቸውን እንዲያቆሙ ከታዘዙም በኋላ እንኳን ‘ወንጌሉን ማስተማርንና መስበክን አልተዉም ነበር።’ (ሥራ 5:40-42) ሐዋርያው ጳውሎስም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በዚህ ሥራ ተካፍሏል። (1 ቆ⁠ሮ. 15:9, 10፤ ቆላ. 1:29) ወንጌሉን የመስበክ ዕዳ እንዳለበት የተሰማው ሲሆን ይህንንም ለመፈጸም ሲል የግል ምቾቱን ለመተው ፈቃደኛ ነበር።​—⁠ሥራ 20:24፤ ሮሜ 1:14-16

4 ወንጌሉን የመስበክ መብታችን:- በአደራ ለተሰጠን ቅዱስ ተልዕኮ ያለን አድናቆት በስብከቱ ሥራ የምናደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉንን አጋጣሚዎች እንድንፈልግ ያነሳሳናል። (ሮሜ 15:15, 16) ያለ ተሽከርካሪ ወንበር መንቀሳቀስ የማይችለው ኤድዋርድ በአንድ ሆቴል ደጃፍ ላይ ተቀምጦ በሆቴሉ ላረፉት ሰዎች ስለ እምነቱ ይነግራቸው ነበር። ሆኖም ይበልጥ ማገልገል ስለፈለገ ለእርሱ የሚመቸው ለየት ያለ መኪና አሠርቶ በሺህ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በመጓዝ ለበርካታ ዓመታት በአቅኚነት አገልግሏል። እንደ ኤድዋርድ ሁሉ ዛሬም ብዙዎች ወንጌሉን ለሌሎች በማሰራጨቱ ሥራ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ ሲሉ አንዳንድ ማስተካከያዎችን አድርገዋል።

5 እንደ ኢየሱስና ሐዋርያቱ እኛም ለስብከቱ ሥራ ሁልጊዜ ቅድሚያ እንስጥ። እንዲህ ካደረግን ሰዎችን እንደምንወድና በአደራ ለተሰጠን ወንጌል አድናቆት እንዳለን እናሳያለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ