የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/03 ገጽ 12
  • ቅድሚያ የምትሰጡት ለምን ነገሮች ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቅድሚያ የምትሰጡት ለምን ነገሮች ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ተቀዳሚ ሥራችን የሆነው ክርስቲያናዊ አገልግሎት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ‘በጌታ የተቀበልከውን አገልግሎት ለመፈጸም ትኩረት ስጥ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • “ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 2/03 ገጽ 12

ቅድሚያ የምትሰጡት ለምን ነገሮች ነው?

1 ብዙ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ትምህርት ቤቶችን ወይም ክሊኒኮችን እንደ መክፈት ለመሳሰሉት የበጎ አድራጎት ተግባራት ትኩረት ይሰጣሉ። የይሖዋ ምሥክሮች ግን ‘መልካም ማድረግና ለሌሎች ማካፈል’ እንዳለባቸው ባይዘነጉም ይበልጥ ቅድሚያ የሚሰጡት ሰዎችን በመንፈሳዊ ለመርዳት ነው።​—⁠ዕብ. 13:16

2 ኢየሱስና ሐዋርያቱ የተዉልን አርዓያ:- ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ብዙ በጎ ተግባራትን ቢያከናውንም ዋነኛ ሥራው ግን ስለ እውነት መመስከር ነበር። (ሉቃስ 4:43፤ ዮሐ. 18:37፤ ሥራ 10:38) ተከታዮቹን “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ . . . እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” በማለት አዟቸዋል። (ማቴ. 28:19, 20) በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ እሱ የጀመረውን ሥራ በበለጠ ስፋት እንደሚያከናውኑም ተናግሯል። (ዮሐ. 14:12) ኢየሱስ ለስብከቱ ሥራ ቅድሚያ ይሰጥ የነበረው ይህ ሥራ ሰዎች የመዳንን መንገድ እንዲማሩ ስለሚረዳ ነው።​—⁠ዮሐ. 17:3

3 ሐዋርያው ጳውሎስ የስብከት ሥራውን እንደ ‘ግዴታ’ ማለትም ችላ ሊባል እንደማይገባው አስፈላጊ ነገር አድርጎ ይመለከተው ነበር። (1 ቆ⁠ሮ. 9:16, 17) አገልግሎቱን ለማከናወን ሲል ማንኛውንም መሥዋዕትነት ለመክፈልና የትኛውንም ዓይነት ፈተና ወይም ችግር ለመጋፈጥ ፈቃደኛ ነበር። (ሥራ 20:22-24) ሐዋርያው ጴጥሮስና የእምነት አጋሮቹም የዚህ ዓይነት ዝንባሌ ነበራቸው። እስራትና ግርፋት ቢደርስባቸውም “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።”​—⁠ሥራ 5:40-42

4 እኛስ? የመንግሥቱን ምሥራች ለማወጅና ደቀ መዛሙርት ለማድረጉ ሥራ ቅድሚያ እንሰጣለን? እንደ ኢየሱስ ‘እረኛ እንደሌላቸው በጎች ለተጨነቁትና ለተጣሉት’ ከልብ እናዝናለን? (ማቴ. 9:36) በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እየተፈጸሙ ያሉት ክስተቶችና የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት የዚህ ክፉ ሥርዓት ማክተሚያ እየቀረበ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣሉ! የስብከቱን ሥራ አስፈላጊነት ሁልጊዜ ማስታወሳችን በቅንዓት ለመስበክ ያነሳሳናል።

5 ሁኔታዎቻችሁን በጥሞና መርምሩ:- የግል ሁኔታዎቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስለሚለዋወጡ በስብከቱ ሥራ የምናደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉንን ማስተካከያዎች ማድረግ እንችል እንደሆነ በየ​ጊዜው ሁኔታዎቻችንን መመርመራችን ተገቢ ነው። አንዲት እህት በ1950ዎቹ፣ 60ዎቹና 70ዎቹ የዘወትር አቅኚ የነበረች ብትሆንም በጤና እክል ምክንያት ለማቆም ተገደደች። ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ ሕመሟ ተሻላት። በቅርቡ ሁኔታዋን ስትመረምረው አቅኚ ሆና ማገልገል እንደምትችል ተገነዘበች። በ90 ዓመት ዕድሜዋ በአቅኚዎች የአገልግሎት ትምህርት ቤት የመካፈል አጋጣሚ በማግኘቷ ምንኛ ተደስታ ይሆን! አንተስ? ጡረታ የምትወጣበት ወይም ትምህርት የምታጠናቅቅበት ጊዜ እየተቃረበ ነው? ይህ ለውጥ አቅኚ ለመሆን ያስችልህ ይሆን?

6 ኢየሱስ፣ ማርታ ‘በሥራ ብዛት ትባክን እንደነበር’ ባስተዋለ ጊዜ ነገሮችን ቀላል በማድረግ ብዙ በረከቶችን ማጨድ እንደምትችል በደግነት ሐሳብ ሰጥቷታል። (ሉቃስ 10:40-42 አ.መ.ት ) ኑሮህን ቀላል ማድረግ ትችላለህ? ባልም ሚስትም ሰብዓዊ ሥራ መሥራታቸው በእርግጥ አስፈላጊ ነው? አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማድረግ ቤተሰቡ በአንድ ሰው ገቢ መተዳደር ይችል ይሆን? ብዙዎች በአገልግሎት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ ማስተካከያዎችን በማድረጋቸው ብዙ መንፈሳዊ በረከቶችን አግኝተዋል።

7 ሁላችንም ኢየሱስና ሐዋርያቱ የተውትን አርዓያ የምንከተል እንሁን! የመንግሥቱን ምሥራች ለመስበክ በሚደረገው ወሳኝ ሥራ እንደ አቅማችን ለመሳተፍ ከልብ ጥረት ካደረግን ይሖዋ እንደሚባርከን እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን።​—⁠ሉቃስ 9:57-62

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ