የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሚያዝያ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 (4)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የቀረቡት የመግቢያ ሐሳቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ በእነዚህ መግቢያዎች በመጠቀም የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች መግቢያዎችን መጠቀም ይቻላል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው በመንገድ ላይ ምሥክርነት ሲሰጥ የሚያሳይ ይሁን።
15 ደቂቃ:- “በስብከቱ ሥራ ጽኑ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሰው ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
15 ደቂቃ:- “መልካም ማድረግንና ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለጉባኤው እንደሚስማማ አድርገህ አቅርበው። ሌሎችን መርዳት የምንችልባቸውን ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መንገዶች ተናገር።
መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 8።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ አስፋፊ ለአዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው “እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች” የተባለውን ብሮሹር ሲሰጠው የሚያሳይ አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊው በገጽ 14 ላይ የሚገኘውን ሥዕል ያሳየውና ስለ ሕዝብ ስብሰባ በአጭሩ ያብራራለታል። ከዚያም በዚያ ሳምንት የሚቀርበውን የሕዝብ ንግግር ርዕስ ይነግረውና በስብሰባው ላይ እንዲገኝ ይጋብዘዋል።
15 ደቂቃ:- የኤሌክትሮኒክ መልእክት መለዋወጫ ዘዴዎች በተስፋፉበት ዘመን ጤናማ አስተሳሰብ መያዝ። (ቲቶ 2:11, 12) በመስከረም 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ከአንቀጽ 1-6 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ።
መዝሙር 75 (169) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 21 (46)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የተላከለት መዋጮ የደረሰው መሆኑን ገልጾ ከሆነ ይህን ጨምረህ አቅርብ። አስፋፊዎች የሚያዝያ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። ለአገልግሎት ክልላችሁ የሚስማማ ከሆነ በገጽ 6 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም የየካቲት 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች መግቢያዎችን መጠቀም ይቻላል። ሠርቶ ማሳያው ውይይቱን ለማስቆም “ፍላጎት የለኝም” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን። (ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 16ን ተመልከት።) በክልሉ ውስጥ ላሉ ሰዎች ይበልጥ ተስማሚ የሆኑ ርዕሶችን ጥቀስ።
30 ደቂቃ:- “ከይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ።” ከ2005 የዓመት መጽሐፍ ላይ የተወሰደው ይህ ደብዳቤ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት ይቀርባል።
መዝሙር 4 (8) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 63 (148)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “የጥያቄ ሣጥን።” አንድ ሽማግሌ ከመጋቢት 15, 1982 መጠበቂያ ግንብ “የአንባቢያን ጥያቄዎች” ላይ የተወሰደውን ይህን ክፍል አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገረ በኋላ በጥያቄና መልስ ያቀርበዋል። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አንቀጽ 1, 2, 4, 5 እና 6ን አንብብ። ከዚህ ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች መጠቀም ትችላለህ:- (1) በ1 ቆሮንቶስ 7:39 ላይ ላለው ምክር ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል? (2) አብርሃም፣ ይስሐቅ ይሖዋን የምትፈራ ሚስት እንዲያገኝ ያን ያህል ጥረት ያደረገው ለምንድን ነው? (3) እንደ ማስጠንቀቂያ ሆኖ የሚያገለግለን የማን ተሞክሮ ነው? (4) ዘዳግም 7:2-4 ምን ማስጠንቀቂያ ይዟል? (5) የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ተመሳሳይ ምክር ተሰጥቷቸው ነበር? (6, 7) (ሀ) አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ በጌታ ብቻ ማግባትን አስመልክቶ የሚሰጠውን ምክር ችላ ቢል በጉባኤ ያሉ ወንድሞችና እህቶች በተለይም ልዩ የአገልግሎት መብት ያላቸው ሁሉ በዚህ ረገድ ክርስቲያናዊ ታማኝነታቸውን መጠበቅ የሚኖርባቸው እንዴት ነው? (ለ) አንድ የይሖዋ ምሥክር ልጁ ወይም ዘመዱ አማኝ ያልሆነ ሰው ለማግባት ቢወስን ለሠርጉ አንዳንድ ዝግጅቶችን ማድረጉም ሆነ መደገሱ እንዲሁም ወንድሞች በዚህ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ መጋበዙ ተገቢ ይሆናል? ወንድሞችስ ቢጋበዙ መገኘት ይኖርባቸዋል?
20 ደቂቃ:- “ሁሉም ዓይነት ሰዎች ይድናሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ትምህርቱን ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል እንደሚስማማ አድርገህ አቅርበው።
መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።