የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/06 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 9 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 16 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 23 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 30 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 6 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 1/06 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥር 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 5 (10)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው በንግድ አካባቢዎች ሲሰብክ የሚያሳይ ይሁን።

15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ​—⁠መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የምንጠቀምበት ዋነኛ ጽሑፍ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ወንድሞች በአዲሱ መጽሐፍ ጥናት ለማስጀመር እንዲጥሩ አነሳሳቸው።

20 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ጥናት ማስጀመር የሚቻልበት መንገድ።” በገጽ 3 ላይ በሚገኘው አባሪ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይትና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ በመጠቀም ወዲያውኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር ብሎም በቀጣይነት መምራት እንጀምራለን። ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ (1) ገጽ 4-5ን፣ (2) ገጽ 6ን እንዲሁም (3) ገጽ 7 ላይ ያለውን አንቀጽ በመጠቀም እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሦስት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። እያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ ከመቅረቡ በፊት ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ተናገር፤ ከቀረበ በኋላ ደግሞ ነጥቦቹን ከልስ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከተባለው መጽሐፍ የምትሸፍኗቸውን አንቀጾች ቁጥር እንደ ሁኔታው ማሳጠር ይቻላል። ሁሉም ሠርቶ ማሳያዎች የሚደመደሙት አስፋፊው ለሚቀጥለው ተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ሲጥል በማሳየት ይሆናል።

መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 71 (163)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ከሁለት ሳምንት በኋላ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና—የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር የተባለውን የቪዲዮ ፊልም ተመልክተው እንዲመጡ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 4-7 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ገጽ 4 ላይ ያለውን ሐሳብ ከሦስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደ መግቢያ ካቀረብክ በኋላ ከገጽ 5 እስከ ገጽ 7 ንዑስ ርዕስ ድረስ ከአድማጮች ጋር ተወያዩበት። የተደራጀ ሕዝብ የተባለው መጽሐፍ ሌሎች ክፍሎች ወደፊት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይቀርባሉ።

20 ደቂቃ:- “እንደ ከዋክብት የሚያበሩ ወጣቶች።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ወጣቶች በትምህርት ቤት እንዴት ምሥክርነት እንደሚሰጡ ጠይቃቸው። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት ወጣቶች አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።

መዝሙር 46 (107) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 83 (187)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ ሌላ አቀራረብ በመጠቀም የኅዳር 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያውን አንድ ወጣት አስፋፊ እንዲያቀርበው አድርግ።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ጥያቄ በመጠየቅና በማዳመጥ ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 2ን ስትወያዩ አድማጮች ውይይት ለመጀመር ውጤታማ ሆነው ያገኟቸውን ጥያቄዎች እንዲናገሩ ጋብዛቸው። አንድ አስፋፊ የቤቱ ባለቤት ሐሳብ እንዲሰጥ ለማድረግ ጥያቄዎችን እንዴት በዘዴ እንደሚጠቀም ከዚያም በትኩረት ሲያዳምጠው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 100 (222)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥር ወር ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በየካቲት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። እንዲሁም አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ለጥቅማችን ተብሎ የተደረገ ፍቅራዊ ዝግጅት። በጉባኤ ሽማግሌ የሚቀርብ። ቅርንጫፍ ቢሮው የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴና የሕሙማን ጠያቂ ቡድን ከሚሰጡት አገልግሎት እንዴት ጥቅም ማግኘት እንደሚቻል ለሁሉም ጉባኤዎች የጻፈውን የጥር 3, 2006 ደብዳቤ አንብብና አብራራ።

20 ደቂቃ:- “አስፈላጊ በሆነ የሕክምና ዘዴ ላይ ያተኮረ የቪዲዮ ፊልም።” የሐዋርያት ሥራ 15:​28, 29ን አንብብና ክርስቲያኖች ደም የማይወስዱበት ምክንያት አምላክ የደምን ቅድስና አስመልክቶ ያወጣውን ሕግ ለመታዘዝ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ መሆኑን አጉላ። ከዚያም የሕሙማን መብትና ፍላጎት የተባለውን ቪዲዮ ለመከለስ የተዘጋጁትን ጥያቄዎች በመጠቀም ውይይቱን ጀምር። ውይይቱን የመጨረሻውን አንቀጽ በማንበብ ደምድም።

መዝሙር 20 (45) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 38 (85)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

25 ደቂቃ:- ከአዲሱ የማስተማሪያ መሣሪያችን ጋር መተዋወቅ። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከተባለው መጽሐፍ የወደዱትን ገጽታ በተመለከተ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ለምሳሌ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ላይ የሚገኙ ዋና ዋና ነጥቦችን የሚያጎሉት የመግቢያ ጥያቄዎችና የክለሳ ሣጥኑ (ገጽ 106, 114)፣ ለማስተማሪያነት የቀረቡት ሥዕላዊ መግለጫዎች (ገጽ 122-123, 147, 198) እንዲሁም ተጨማሪው ክፍል (ገጽ 197 አን. 1-2)። የዚህ መጽሐፍ አቀራረብ የሚያጓጓና የሚያስደስት ነው (ገጽ 12 አን. 12)። ቀላልና ግልጽ ማብራሪያዎች ይሰጣል (ገጽ 58 አን. 5) እንዲሁም ውጤታማ ምሳሌዎችን ይጠቀማል (ገጽ 159 አን. 12)። መቅድሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር እንድንችል እኛን ለመርዳት ተብሎ የተዘጋጀ ነው (ገጽ 3-7)። ለአንድ አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ገጽ 7 ላይ ያለውን ሣጥን እንዴት ማስረዳት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አዲሱን መጽሐፍ በመጠቀም የተገኙ ተሞክሮዎችን ተናገር።

10 ደቂቃ:- ረዳት አቅኚነት በረከት ያስገኛል። (ምሳሌ 10:​22) ባለፈው ዓመት በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ያገለገሉ አስፋፊዎች ፕሮግራማቸውን እንዴት እንዳስተካከሉና በመጨረሻም ያገኙትን በረከት እንዲናገሩ ጋብዝ። በዚህ ዓመት በመጋቢት፣ በሚያዝያ እንዲሁም በግንቦት ረዳት አቅኚ ሆነው ማገልገል ይችሉ እንደሆነ በጸሎት እንዲያስቡበት ሁሉንም አበረታታ።

መዝሙር 93 (211) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ