የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 29, 2008 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከኅዳር 3 እስከ ታኅሣሥ 29, 2008 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
የንግግር ባሕርይ
1. “በፍቅር” ላይ ተመሥርቶ ምክር መስጠት የሰዎችን ልብ ይነካል የምንለው ለምንድን ነው? (ፊል. 9) [be ገጽ 266 አን. 1-3]
2. ሌሎችን ማበረታታት የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 268 አን. 4 እስከ ገጽ 269 አን. 1]
ክፍል ቁ. 1
3. ጳውሎስ ለቲቶ የጻፈለት ደብዳቤ በዛሬው ጊዜ ለምንገኝ ክርስቲያኖች ‘መልካምና ጠቃሚ’ የሆነው በምን መንገድ ነው? (ቲቶ 3:8) [bsi08-2 ገጽ 11 አን. 8]
4. ጴጥሮስ የጻፈው የመጀመሪያ መልእክት ወቅታዊ ነበር የምንለው ለምንድን ነው? [bsi08-2 ገጽ 19 አን. 1]
5. በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት ምሳሌያዊ መግለጫዎች ምን ዓይነት ስሜት ሊያሳድሩብን ይገባል? [bsi08-2 ገጽ 29 አን. 1]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
6. ጳውሎስ በቲቶ 2:3 ላይ ‘ስም የማያጠፉ’ የሚለውን ሐሳብ “በወይን ጠጅ ሱስ የተጠመዱ እንዳይሆኑ” ከሚለው ሐሳብ ጋር አያይዞ የጠቀሰው ለምን ሊሆን ይችላል? [w94 6/15 ገጽ 20 አን. 12]
7. ሰይጣን “በሞት ላይ ኀይል” እንዳለው መገለጹ የፈለገውን ሰው ሁሉ መግደል እንደሚችል የሚያሳይ ነው? (ዕብ. 2:14) [w08 10/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—ለቲቶና ለፊልሞና እንዲሁም ለዕብራውያን ክርስቲያኖች የተጻፉት ደብዳቤዎች ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
8. ከአዲሱ ቃል ኪዳን ጋር በተያያዘ “ቃል ኪዳኑን የገባው ሰው” የተባለው ማን ነው? (ዕብ. 9:16 NW) [w08 10/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—ለቲቶና ለፊልሞና እንዲሁም ለዕብራውያን ክርስቲያኖች የተጻፉት ደብዳቤዎች ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
9. ሰላማውያን መሆን ሲባል ምን ማለት ነው? ከዚህ ጋር በተያያዘ ራሳችንን ምን ብለን መጠየቅ እንችላለን? (ያዕ. 3:17) [w08 3/15 ገጽ 24 አን. 18]
10. “[አምላክ] ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው” የሚለው አገላለጽ ምን ትርጉም አለው? (1 ዮሐ. 3:20) [w05 8/1 ገጽ 30 አን. 19]