መጋቢት 30 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 1-6
ቁ. 1፦ ዘፀአት 1:1-19
ቁ. 2፦ ኢየሱስ እንድንጸልይ አስተምሮናል (lr ምዕ. 12)
xቁ. 3፦ በዘመናችን የሚደረገው ፈውስ በአምላክ መንፈስ እርዳታ የሚከናወን ነው? (rs ገጽ 157 አን. 2 እስከ 158 አን. 2)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 32 (70)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከት ማስታወቂያ ካለ ተናገር።
15 ደቂቃ፦ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙትን ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ለመርዳት ዝግጁ ሁኑ። በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን፣ የቀዘቀዙ አስፋፊዎችንና ሌሎችን (የምናውቃቸው ሰዎች፣ ዘመድ አዝማዶችና የቤተሰብ አባሎች ሊሆኑ ይችላሉ) በመርዳት ረገድ አስፋፊዎች የሚኖራቸውን ድርሻ በተመለከተ በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። (የመጋቢት 2008 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6ን ተመልከት።) በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኘን ፍላጎት ያለው ግለሰብ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ይኸውም ከእሁድ ሚያዝያ 5 ጀምሮ የሚነበቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉም እንዲያነቡ አሳስባቸው። ይህን ማድረግ የሚቻልባቸውን አንዳንድ ተግባራዊ ሐሳቦች መለገስ ይቻል ይሆናል።
15 ደቂቃ፦ “መጽሐፍ ቅዱስ—የእውነትና የትንቢት መጽሐፍ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።
መዝሙር 95 (213)
[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሚያዝያ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 16 (37)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 7-10
ቁ. 1፦ ዘፀአት 9:1-19
ቁ. 2፦ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት (lr ምዕ. 13)
ቁ. 3፦ ገላትያ 6:2ን ከገላትያ 6:5 ጋር የምናስማማው እንዴት ነው?
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 38 (85)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ የሚቻለው እንዴት ነው? በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 255 እስከ 257 ላይ ተመሥርቶ ሞቅ ባለ ስሜት በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
20 ደቂቃ፦ ወጣቶች—በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል? አንድ ሽማግሌ በዚህ ርዕስ የተዘጋጀውን ትራክት መሠረት አድርጎ ከአድማጮች ጋር ይወያያል። መንግሥቱን ለማስቀደም የሚጥሩ የተጠመቁ ወጣቶችን ከልብ አመስግናቸው። ከወጣትነቱ ጀምሮ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለተካፈለ ወይም በልጅነቱ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመካፈል ግብ አውጥቶ አሁን በዚህ የአገልግሎት ዘርፍ ለሚካፈል አንድ አስፋፊ አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። ‘ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመግባት ያነሳሳህ ምንድን ነው? በዚህ አገልግሎት በመካፈልህ ምን በረከቶችን አግኝተሃል?’
መዝሙር 33 (72)