የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/10 ገጽ 2
  • ‘መጥተህ ተከታዬ ሁን’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘መጥተህ ተከታዬ ሁን’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘መጥተህ ተከታዬ ሁን’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው”
    “ተከታዬ ሁን”
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • “ተከታዬ ሁን”—ኢየሱስ ምን ማለቱ ነበር?
    “ተከታዬ ሁን”
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
km 2/10 ገጽ 2

‘መጥተህ ተከታዬ ሁን’

1. የኢየሱስን ምሳሌ ለመከተል ልዩ አጋጣሚ የሚፈጥርልን የትኛው ሥራ ነው?

1 አራቱ የወንጌል ዘገባዎች የአምላክ ልጅ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት ዝርዝር መረጃዎች ይሰጡናል። እኛ ክርስቲያኖች ‘የኢየሱስን ፈለግ በጥብቅ መከተል’ ስላለብን በአገልግሎታችን ሊያበረታቱን ለሚችሉ የኢየሱስ ሕይወት ገጽታዎች ለየት ያለ ትኩረት ሰጥተን መመርመራችን አስፈላጊ ነው።—1 ጴጥ. 2:21፤ ማር. 10:21

2. ኢየሱስ የተወው የጽናት ምሳሌ እኛን የሚጠቅመን እንዴት ነው?

2 ኢየሱስ የተወልን ምሳሌ፦ ከቤት ወደ ቤት ስታገለግሉ ሰዎች መጥፎ ምላሽ ሰጥተዋችሁ ያውቃሉ? እንዲህ ያለ ምላሽ ሲያጋጥመን ኢየሱስ “እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል” በማለት የተናገረው ሐሳብ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንገነዘባለን። (ዮሐ. 15:20) እርግጥ ነው፣ የሚያጋጥመን መጥፎ ምላሽ በሙሉ ስደት ነው ማለት አይደለም። ይሁንና ኢየሱስ የደረሰበትን የተለያየ ፈተናና ስደት በጽናት መቋቋም የቻለው ከፊት ለፊቱ የነበረውን ደስታ በትኩረት ይመለከት ስለነበር ነው። እኛም በተመሳሳይ ትኩረታችንን የይሖዋን ሞገስ በማግኘታችንና ታማኝ ሆነን በምናገኘው ሽልማት ላይ ማድረግ እንችላለን። ይህ ደግሞ ‘እንዳንደክምና በነፍሳችን እንዳንዝል ይረዳናል።’ (ዕብ. 12:2, 3፤ ምሳሌ 27:11) በአገልግሎት ስንጸና ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚደግፈን መተማመን እንችላለን።—ማቴ. 28:20

3. ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ኢየሱስን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?

3 “የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው”፦ በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ የመጀመሪያውን ቦታ የያዘው ስለ መንግሥቱ የመስበኩ ሥራ ነበር። (ሉቃስ 4:43) ኢየሱስ ምንም ሳይሰስት ራሱን ለአገልግሎቱ ሰጥቷል። አገልግሎቱን አጣዳፊ እንደሆነ አድርጎ ይመለከተው ስለነበር ሁልጊዜ ስለ መንግሥቱ ለመናገር የሚያስችለውን አጋጣሚ ይፈልግ ነበር። የኢየሱስ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን የእሱን ፈለግ መከተል ምን እንድናደርግ ያነሳሳናል? የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችንን ስናከናውን ምሥራቹን ልናካፍላቸው የምንችላቸው ሰዎች አሉ? ለክርስቶስ ያለን ፍቅር ምሥራቹን በተቻለን መጠን በስፋት ለማሰራጨት ሊያነሳሳን ይገባል።—2 ቆሮ. 5:14

4. የአገልግሎታችንን ጥራት ማሻሻል የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?

4 “ማንም እንደዚህ ሰው ተናግሮ አያውቅም”፦ ኢየሱስ ያስተማረበት መንገድ አድማጮቹን አስገርሟቸዋል። (ዮሐ. 7:46፤ ማቴ. 7:28, 29) ኢየሱስ ከሌሎች አስተማሪዎች የተለየ እንዲሆን ያደረገው ምንድን ነው? ያስተምረው ለነበረው እውነትና ለሚያስተምራቸው ሰዎች ፍቅር ነበረው፤ እንዲሁም የተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎችን ይጠቀም ነበር። ታላቁን አስተማሪ በመምሰል የአገልግሎታችንን ጥራት ማሻሻል እንችላለን።—ሉቃስ 6:40

5. የክርስቶስ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን ግባችን ምን መሆን አለበት?

5 ኢየሱስ ያሳለፈውን ሕይወት በመመርመር ከሚገኙት ውድ ሀብቶች ጥቂቶቹን ተመልክተናል። ከዚህ በተጨማሪ ምን ሌላ ውድ ሀብት ማግኘት ትችላላችሁ? ስለ ኢየሱስ ሕይወት የሚናገሩ ታሪኮችን ስትመረምሩ በቃልም ሆነ በድርጊት የተወውን ምሳሌ በመከተል ‘የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ’ ግብ ይኑራችሁ።—ኤፌ. 3:19

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ