መጋቢት 15 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 5-9
ቁ. 1፦ 1 ሳሙኤል 6:1-9
ቁ. 2፦ የሰይጣንንና የአጋንንቱን ጥቃት የምንመክትበት ምን መከላከያ አለን?
ቁ. 3፦ ስለ ሀብታሙ ሰውና ስለ አልዓዛር የሚናገረው ምሳሌ ትርጉም ምንድን ነው? (rs ገጽ 175 አን. 2 እስከ ገጽ 176 አን. 1)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ የ2010ን የዓመት መጽሐፍ በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙበት። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። “ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ” የሚለውን ተወያዩበት። ከዓመት መጽሐፉ ላይ አንዳንድ ተሞክሮዎችን በመምረጥ ተሞክሮዎቹ በአገልግሎታችን እንዴት እንደሚያበረታቱን ግለጽ። አድማጮች ከዓለም አቀፉ ሪፖርት ላይ ያስደነቃቸውን ነገር በተመለከተ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ሁሉም የዓመት መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር እንዲያነቡ በማበረታታት ክፍሉን ደምድም።
15 ደቂቃ፦ “ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ የሆነው ሥራ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 3ን ከተወያያችሁ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ እድገት እንዲያደርግ የመርዳት መብት ካገኘ አንድ አስፋፊ ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ምን ለውጦችን ማድረግ አስፈልጎታል? ይህስ አስፋፊው ምን እንዲሰማው አድርጎታል?