ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ መጋቢት፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጽሔቶች፤ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
◼ አዳዲስ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት እትሞች እንደደረሱ ለአስፋፊዎች መሰጠት ይኖርባቸዋል። እንዲህ መደረጉ አስፋፊዎች መጽሔቶቹን በአገልግሎት ላይ ከማበርከታቸው በፊት እንዲያነቧቸው ያስችላቸዋል።
◼ የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ማክሰኞ፣ መጋቢት 30, 2010 (እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መጋቢት 21, 2002) ነው። በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚዘመሩት መዝሙሮች የተወሰዱት ከአዲሱ የመዝሙር መጽሐፍ ላይ ሲሆን ቁጥር 8 እና 5 ናቸው። ጉባኤያችሁ ስብሰባ ማክሰኞ ዕለት የሚያደርግ ከሆነ ይህን ስብሰባ በሳምንቱ ውስጥ ሌላ ቀን ላይ ለማድረግ ጥረት ማድረጉ አስፈላጊ ነው። በመንግሥት አዳራሹ ብዙ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነና ስብሰባውን ወደ ሌላ ቀን ማዛወር ካልተቻለ የጉባኤው ስብሰባ ሊሰረዝ ይችላል። በዚያ ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይቀርቡ የነበሩ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑ ክፍሎችን በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ማካተት ይቻላል።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ የ2009 ዎችታወር ላይብረሪ።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ ኮንኮርዳንስ፣ ኦል ስክሪፕቸርስ፣ ማመራመር፣ የአምላክ ወዳጅ፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የይሖዋ ምሥክሮች—እነማን ናቸው?፣ ዎንደርስ ኦቭ ክርኤሽን (ዲቪዲ)፣ ቱ ዚ ኤንድስ ኦቭ ዚ ኧርዝ (dvea)፣ ኖኀ ኤንድ ዴቪድ (dvnad)፣ ዩናይትድ ባይ ዲቫይን ቲቺንግ (dvun) እና በደም ምትክ የሚሰጡ ሕክምናዎች—ተከታታይ ጥናታዊ ፊልም በዲቪዲ።