ሚያዝያ 5 የሚጀምር ሳምንት
ሚያዝያ 5 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ምዕ. 11 ከአን. 20-22፤ በገጽ 131 ላይ የሚገኘው ሣጥን
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 16-18
ቁ. 1፦ 1 ሳሙኤል 18:1-16
ቁ. 2፦ ከገና በዓል ጋር የተያያዙ ልማዶችን ስንመረምር ምን ምን ነገሮችን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል? (rs ገጽ 178 ከአን. 1-3)
ቁ. 3፦ የእንግዳ ተቀባይነትን ባሕል ማዳበር ያለብን ለምንድን ነው? (ሮም 12:13)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የቤቱ ባለቤት ‘በአምላክ አላምንም’ ቢል ምን ማድረግ ይኖርብናል? ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 151 እስከ 152 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በመታሰቢያው በዓል ላይ ለተገኙ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉላቸው። በንግግር የሚቀርብ። በመታሰቢያው ላይ የተገኙ ተሰብሳቢዎችን ቁጥር ጥቀስ፤ እንዲሁም ከመታሰቢያው በዓል ጋር የተያያዙ ተሞክሮዎችን ተናገር። ወንድሞች በመታሰቢያው በዓል ላይ ለተገኙ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ እንዲያደርጉና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ እንዲያወጡ አበረታታቸው። በተጨማሪም በቅርቡ በሚኖረው ልዩ የሕዝብ ንግግር ላይ እንዲገኙ ሰዎችን ሊጋብዙ ይገባል። ፍላጎት ያለው አንድ ሰው በልዩ የሕዝብ ንግግሩ ላይ እንዲገኝ ግብዣ ሲቀርብለት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።