ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጽሔቶች፤ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?፤ ሐምሌ፦ ብሮሹሮች።
◼ ጉባኤዎች አውራጃና ወረዳ ስብሰባ እንዲሁም የልዩ ስብሰባ ቀን በሚያደርጉባቸው ሳምንታት የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት እና የአገልግሎት ስብሰባ አያደርጉም። በመሆኑም በእነዚህ ሦስት ስብሰባዎች ላይ ይቀርቡ የነበሩትን ትምህርቶች በግላችሁ ለምሳሌ፣ በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁ ላይ እንድትወስዷቸው ሁላችሁንም እናበረታታችኋለን።
◼ በ2010 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ ንግግር ርዕስ “እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት የሚገኘው መቼ ነው?” የሚል ነው።