ግንቦት 31 የሚጀምር ሳምንት
ግንቦት 31 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 16-18
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል 17:1-13
ቁ. 2፦ ኢየሱስ “የሰንበት ጌታ” የተባለው ለምንድን ነው? (ማቴ. 12:8)
ቁ. 3፦ አምላክን ያማልዳሉ ብለን “ለቅዱሳን” ልዩ አክብሮት ልንሰጣቸው ይገባናል? (rs ገጽ 184 አን. 9 እስከ ገጽ 185 አን. 5)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ “በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት እንደሚካሄድ ለሰዎች አሳይታችሁ ታውቃላችሁ?” በንግግር የሚቀርብ። በርዕሱ ውስጥ የተሰጠውን ሐሳብ ካብራራህ በኋላ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “አዲሶች እንዲሰብኩ ማሠልጠን የሚቻልበት መንገድ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 5ን ከተወያያችሁ በኋላ አንድ ሽማግሌ ከአዲስ አስፋፊ ጋር ሲያገለግል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አዲሱ አስፋፊ አቀራረቡን ተጠቅሞ የቤቱን ባለቤት ያነጋግራል፤ ሆኖም ጥቅስ ለማንበብ አልሞከረም። ከበሩ ዞር ካሉ በኋላ ሽማግሌው በዘዴና በደግነት መንፈስ ከቤት ወደ ቤት ሲያገለግል መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠቀም አዲሱን አስፋፊ ያበረታታዋል።