የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ የአገልግሎት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ 8,692 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር በመገኘቱ በጣም ተደስተናል! ምንም እንኳ የየካቲት ወር አጭር ቢሆንም በየጉባኤዎቻችን የሚገኙ አስፋፊዎችና ረዳት አቅኚዎች ከፍተኛ የአገልግሎት እንቅስቃሴ አድርገዋል። ብዙ አስፋፊዎች ያልተሠሩ ክልሎችን ለመሸፈን በተደረገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ የተካፈሉ ሲሆን በርካታ አስደሳች ተሞክሮዎችን አግኝተዋል። አንዳንድ አስፋፊዎች በሄዱባቸው ክልሎች ውስጥ የእነሱን መምጣት የሚጠባበቁ በርከት ያሉ ሰዎችን ያቀፉ ቡድኖች አግኝተዋል፤ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች እየተከተሏቸው አምላክ ለእኛ ስላለው ዓላማ እንዲያስተምሯቸው ለምነዋቸዋል! ሁለት ጊዜያዊ ልዩ አቅኚዎች ከሃምሳ በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን እየመሩ ነው! ከዚህም በላይ አጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር ከጥር ወር ጋር ሲነጻጸር ከ200 በላይ መጨመሩ የሚያስደስት ነው። በምናገኘው አጋጣሚ ሁሉ አዳዲስ ጥናቶችን ለማስጀመር ጥረት እያደረግን ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ሙሉ ትኩረት መስጠታችንን እንቀጥል!