የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
አዲሱን የአገልግሎት ዓመት 9,023 በደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ጀምረናል። በተጨማሪም የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት አማካይ የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፤ በመስከረም ወር 1,382 የሆነ አዲስ ከፍተኛ የአቅኚዎች ቁጥር ተመዝግቧል። ከእነዚህ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች መካከል 283 የሚሆኑት በነሐሴ ወር በአቅኚዎች የአገልግሎት ትምህርት ቤት ተካፍለዋል። በትምህርት ቤቱ ከተካፈሉት መካከል 112ቱ ተሞክሮ ያካበቱ አቅኚዎች ኮርሱን የወሰዱት ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመርና መምራት ልንዘነጋው የማይገባን ትልቁ ግባችን ነው።