መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
ዘፍጥረት 2:16, 17ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “አንዳንዶች አምላክ፣ አዳም ኃጢአት እንደሚሠራ አስቀድሞ ያውቅ ነበር ይላሉ። ሌሎች ደግሞ አምላክ መጨረሻው ምን እንደሚሆን የሚያውቅ ከሆነ እንዲህ ያለውን ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ግብዝነት እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በዚህ መጽሔት ገጽ 13 ላይ የሚገኘው ርዕስ፣ አምላክ አስቀድሞ የማወቅ ችሎታውን የሚጠቀምበት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ጥር 2011
“አንዳንዶች ሃይማኖታዊ እምነቶች የተመሠረቱት በምክንያታዊ አስተሳሰብ ላይ ሳይሆን በጭፍን እምነት ላይ እንደሆነ ያምናሉ። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖታዊ እምነት በጭፍን አሜን ብለው የሚቀበሉት መሆን እንደሌለበት ይናገራል። [1 ዮሐንስ 4:1ን አንብብ።] በዚህ መጽሔት ገጽ 28 ላይ የሚገኘው ርዕስ፣ እምነትህ በምክንያታዊ አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ማረጋገጥ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“በዛሬው ጊዜ ፍቺ በጣም የተለመደ ሆኗል። ለፍቺ መበራከት ዋነኛው ምክንያት ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በርካታ ባለትዳሮች ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን ምክር ላሳይዎት። [1 ቆሮንቶስ 10:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ባለትዳሮች የሚያነሷቸውን ስድስት የተለመዱ ቅሬታዎች ይጠቅሳል እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ ችግሮቹን ለመፍታት የሚረዳው እንዴት እንደሆነ ይዳስሳል።”
ንቁ! የካቲት 2011
“በመናፍስታዊ ድርጊቶች፣ በሟርትና በጥንቆላ የሚካፈሉ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ የመጣ ይመስላል። እርስዎስ በመናፍስታዊ ድርጊቶች መካፈል ምንም ጉዳት እንደማያስከትል ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አምላክ ጥንት ለነበሩት እስራኤላውያን የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ላንብብልዎት። [ዘዳግም 18:10-12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ መናፍስታዊ ድርጊቶችን አስመልክቶ ምን እንደሚል ያብራራል።”