መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“አምላክ ሁሉንም ጸሎቶች ይሰማል ብለው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ ይህን በተመለከተ ምን እንዳለ ልብ ይበሉ። [ማቴዎስ 6:7ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ከጸሎት ጋር በተያያዘ ብዙውን ጊዜ ለሚነሱ አራት ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መልስ ይሰጣል።” በገጽ 16 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! የካቲት 2009
“ብዙ ሰዎች ዕድላችን አስቀድሞ ተወስኗል ብለው ያምናሉ። ይህን ጉዳይ በተመለከተ እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ጥቅስ ሁላችንም የመምረጥ ነፃነት እንዳለን ያሳያል። [ዘዳግም 30:19ን አንብብ።] ይህ ርዕስ አስቀድሞ ዕድላችን ተወስኗል ስለሚለው አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚናገር ይገልጻል።” በገጽ 12 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ነገሮች በሙሉ አስቀድመው የተወሰኑ ናቸው ብለው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] [ከገጽ 4 ላይ መክብብ 9:11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ አምላክ ምድር ውብ የሆነች መኖሪያ እንድትሆን አስቀድሞ የወሰነ ቢሆንም እያንዳንዳችን ለሕይወታችን ይጠቅመናል የምንለውን ነገር የመምረጥ ነፃነት እንደሰጠን ይገልጻል።”
ንቁ! መጋቢት 2009
“ብዙዎች በተለይ የኢኮኖሚ ውድቀት ባለበት በዛሬው ጊዜ ስለ ገንዘብ ይጨነቃሉ ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ሚዛናዊነት የሚንጸባረቅበትን ይህን ምክር ልብ ይበሉ። [1 ጢሞቴዎስ 6:8, 10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ገንዘባችንን የአእምሮ ሰላም በሚያስገኝልን መንገድ እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚገልጹ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ይዟል።”