መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“አንዳንድ ጽሑፎች ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ በሚለው መንገድ እንዳልሞተ እንዲያውም አግብቶ ልጆች ወልዶ እንደነበር ይናገራሉ። እርስዎ እንዲህ ሲባል ሰምተው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ስለዚህ ጉዳይ እውነቱን ማወቃችን አስፈላጊ ነው። [ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ በሚናገረው ሐሳብ ላይ እምነት እንድንጥል የሚያስችሉንን አሳማኝ ማስረጃዎች ይዟል።” በገጽ 26 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሚያዝያ 2010
መዝሙር 37:9-11ን አንብብ። ከዚያም “ይህ ትንቢት ሲፈጸም ዓለም ምን መልክ የሚኖረው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕሰ ትምህርት ይህን አበረታች ትንቢት በመጥቀስ አሁን በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ክፋት ይህን ያህል የበዛው ለምን እንደሆነ ያብራራል።” በገጽ 20 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“‘አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምን ይሆን?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ብዙ ሰዎች የሚያነሱትን ጥያቄ እንዴት አድርጎ እንደገለጸው ልብ ይበሉ። [መዝሙር 10:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ መከራን የፈቀደበትን ምክንያት አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንዲሁም ችግሩን ለማስወገድ በአሁኑ ጊዜ ምን በማድረግ ላይ እንደሆነ ይናገራል።”
ንቁ! ግንቦት 2010
“ብዙ ሰዎች ሲጋራ የማቆም ፍላጎት ቢኖራቸውም ይህን ማድረግ ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ሲጋራ ማጨስ ለማቆም የሚፈልግ ሰው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አንዳንዶች ጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው እንዲረዷቸው መጠየቃቸው እንደጠቀማቸው ይናገራሉ። [መክብብ 4:12ሀን አንብብ።] ይህ መጽሔት አንድ ሰው ማጨስ እንዲያቆም የሚረዱትን አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦች ይዟል።”