መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
b“ብዙ ሰዎች በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ሃይማኖቶች ‘ወደ አንድ አምላክ የሚያደርሱ የተለያዩ መንገዶች ናቸው’ የሚል እምነት አላቸው። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [ኢያሱ 24:15ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ሃይማኖታችን በእርግጥ ወደ እውነተኛው አምላክ የሚያደርስ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ በግለሰብ ደረጃ መመርመራችን አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳዩ አሳማኝ ምክንያቶችን ይዟል።” በገጽ 12 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሰኔ 2009
“ሁላችንም የሞቱ ሰዎችን እናውቃለን። ከእነዚህ ሙታን መካከል አንዳንዶቹ ተናደው ጉዳት ያደርሱብናል ብለን መፍራት የሚኖርብን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም መክብብ 9:5, 6ን አንብብ።] በዚህ ርዕሰ ትምህርት ውስጥ የሚያጽናና ሐሳብ እንደሚያገኙ እርግጠኛ ነኝ።” በገጽ 22 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ቢኖራቸውም የመጽሐፍ ቅዱስን ሐሳብ መረዳት በጣም አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። እርስዎስ እንደዚህ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። መዝሙር 119:130ን አንብብ።] ይህ ጥቅስ እንደሚያሳየው መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈው አምላክ ቃሉን እንድንረዳና ከሐሳቡ ጥቅም እንድናገኝ ይፈልጋል። ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ማድረግ የምንችላቸውን ሦስት ነገሮች ይዟል።”
ንቁ! ሐምሌ 2009
“በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች በመንፈስ ጭንቀት ይሠቃያሉ። አምላክ በስሜት ቀውስ ለሚሠቃዩ ለእነዚህ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ የሚያስብላቸው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም መዝሙር 34:18ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመንፈስ ጭንቀት የሚሠቃዩ ሰዎች የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም አምላክ እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ያብራራል። በተጨማሪም እነዚህን ሰዎች ለማጽናናት ምን ማለት እንደምንችል የሚገልጽ ሐሳብ ይዟል።”