መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“ብዙዎቻችን በጠና የታመመ ወይም ለሞት በሚያደርስ በሽታ የተያዘ ጓደኛችንን ለመጠየቅ ስንሄድ ምን እንደምንለው ግራ ይገባናል። ይህ ምክር የሚጠቅመን ይመስሎታል? [ያዕቆብ 1:19ን አንብብ። ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ምክሮችን ይዟል።” በገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሐምሌ 2010
“ሴቶች አገልጋዮች ሆነው መሾም አለባቸው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አንዲት ሴት የሚናገረውን ሐሳብ ይመልከቱ። [ሮም 16:1ን አንብብ።] ሌላ ጥቅስ ደግሞ ሴቶች በጉባኤ ውስጥ ዝም ማለት እንዳለባቸው ይናገራል። ታዲያ በዚህ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ይህ ርዕስ ስለዚህ ጉዳይ ያብራራል።” በገጽ 28 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ብዙ ሰዎች በኑክሌር ጦርነት ወይም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ምድር ትጠፋለች ብለው ይሰጋሉ። እርስዎስ እንዲህ ያለ ሁኔታ ይከሰታል ብለው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [ራእይ 11:18ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የዓለም መጨረሻን በተመለከተ ለሚነሱ አራት የተለመዱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።”
ንቁ! ነሐሴ 2010
“ከዚህ ቀደም ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ተነጋግረው የሚያውቁ ይመስለኛል። ብዙ ሰዎች ለማዳመጥ ፍላጎት ባይኖራቸውም ከቤት ወደ ቤት እየሄድን የምንሰብከው ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ማቴዎስ 24:14ን አንብብ።] ብዙዎች ስለ እኛ የተዛባ አመለካከት እንዳላቸው እናውቃለን። ይህ መጽሔት የይሖዋ ምሥክሮች እነማን እንደሆኑ ይገልጻል።”