መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“በዚህ አስጨናቂ ዘመን ውስጣዊ ሰላም ማግኘት የሚቻል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ በፊልጵስዩስ 4:6, 7 ላይ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ትምህርት አምላክ የሚሰጠውን ሰላም እንዴት ማግኘት እንደምንችል ያብራራል።” በገጽ 10 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሐምሌ 2009
b“አብዛኞቻችን ከወላጆቻችን ላገኘነው ትምህርት በጣም አመስጋኞች ነን። አንድ ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ የተማራቸው ሃይማኖታዊ ትምህርቶች እውነት መሆን አለመሆናቸውን ቢመረምር ለወላጆቹ አክብሮት ሳያሳይ እንደቀረ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም 1 ዮሐንስ 4:1ን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ትምህርት ሃይማኖታችንን መቀየራችን ስህተት መሆን አለመሆኑን ያብራራል።” በገጽ 28 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ አንድ አምላክ የሚያደርሱ የተለያዩ መንገዶች ናቸው ብለው የሚናገሩ ሰዎች አሉ። ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ እንደሆኑ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ማቴዎስ 7:13, 14ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ አንድ ጥሩ ሃይማኖት ሊያስተምራቸው የሚገቡ ሦስት ነገሮችን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ይዟል።”
ንቁ! ነሐሴ 2009
“መድልዎ ተፈጽሞበት የማያውቅ ሰው የለም ማለት ይቻላል። አምላክ ጭፍን ጥላቻን በተመለከተ ምን የሚሰማው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ መድልዎ በሚፈጸምብን ጊዜ ሁኔታውን እንድንቋቋም ሊረዳን ይችላል። እኛም ጭፍን ጥላቻ ካለብን ይህን አስተሳሰብ ከሥሩ ነቅለን ማስወገድ እንድንችል ይረዳናል። ይህ መጽሔት ይህን ጉዳይ ያብራራል።”