መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
ዘፀአት 20:15ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “በርካታ ሰዎች ይህን ትእዛዝ ለመከተል ጥረት ያደርጋሉ። ሆኖም አንዳንዶች አንድ ሰው ከአቅም በላይ በሆኑ ሁኔታዎች የተነሳ ቢሰርቅ ወይም ሌላ ሐቀኝነት የጎደለው ተግባር ቢፈጽም ስህተት እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕሰ ትምህርት ሁልጊዜ ሐቀኛ መሆን ያለውን ጥቅም ያብራራል።” በገጽ 12 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! መጋቢት 2010
“ብዙ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ቢኖራቸውም አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በዘመናችን ላሉ ሰዎች ያን ያህል የሚጠቅም እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ እርስዎ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ሮም 15:4ን አንብብ።] ከተጻፉ በጣም ረጅም ጊዜ የሆናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እንኳ አሁንም ድረስ ጠቃሚ የሆኑት ለምን እንደሆነ ይህ ርዕሰ ትምህርት ያብራራል?።” በገጽ 28 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“በታሪክ ውስጥ ከሁሉ ይበልጥ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረው ማን እንደሆነ ሲጠየቁ ብዙዎች ኢየሱስ እንደሆነ ይናገራሉ። የእርስዎስ መልስ ተመሳሳይ ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እውነትን ለመማር ከፈለግን ኢየሱስን አስመልክቶ ከሚነገሩ እርስ በርስ የሚጋጩ ሐሳቦች መካከል ትክክለኛውን ለይተን ማወቃችን አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ባሳይዎት ደስ ይለኛል። [ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ ልዩ እትም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስና እሱ ስላስተማራቸው ትምህርቶች ምን እንደሚል ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ 2010
“አብዛኞቻችን፣ የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማከናወን በቂ ጊዜ እንደሌለን ይሰማናል። እርስዎስ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙዎች ይህን ምክር ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። [ፊልጵስዩስ 1:10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጊዜያችንን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደምንችል የሚጠቁሙ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ይዟል።”