መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“ሁሉም ሰው በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ኢየሱስ የተናገረውን ይህን ሐሳብ ቢከተል ኖሮ ዓለም ምን ዓይነት ቦታ የምትሆን ይመስልዎታል? [ማቴዎስ 7:12ን አንብብ። ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕስ የኢየሱስ ተከታይ መሆን ማለት ምን ነገሮችን እንደሚጨምር ለማሳየት ኢየሱስ ያስተማራቸውን አንዳንድ ትምህርቶች ያብራራል።” በገጽ 16 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ግንቦት 2010
“የኢኮኖሚው ሁኔታ በቅርቡ የሚስተካከል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች እንዲህ ባለው አስቸጋሪ ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳን እንደሚችል አያውቁም። [በርዕሱ ውስጥ የሚገኝ አንድ ጥቅስ አንብብ።] ይህ ርዕስ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ሲከሰት ችግሩን ለመቋቋም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ምክር እንዴት እንደሚረዳን ያብራራል።” በገጽ 18 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ድሮው ስለ ኃጢአት ሲናገሩ አይደመጥም። እርስዎስ ኃጢአት ጊዜ ያለፈበት ነገር እንደሆነ ይሰማዎታል? ወይስ ሁኔታው ሊያሳስበን ይገባል ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ሮም 5:12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃጢአት ምን እንደሚል ይናገራል።”
ንቁ! ሰኔ 2010
“ሕይወት የሚያስከትለው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ይመስላል። እርስዎስ በዚህ ሐሳብ አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በርካታ ሰዎች ይህ ጥቅስ በዛሬው ጊዜ ውጥረት እየባሰ የሄደበትን አንዱን ምክንያት እንደሚገልጽ ይሰማቸዋል። [2 ጢሞቴዎስ 3:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ውጥረት ምን እንደሚያስከትልብን ያብራራል። በተጨማሪም ያለብን ውጥረት ከቁጥጥራችን ውጪ እንዳይሆን ምን ማድረግ እንደምንችል የሚጠቁሙ አንዳንድ ሐሳቦችን ይዟል።”