መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“ሰዎች ተቃራኒውን እንድናደርግ ተጽዕኖ እያሳደሩብን ትክክለኛውን ነገር ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። በዚህ ተጽዕኖ እንዳንሸነፍ ምን ሊረዳን የሚችል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው፤ ከዚያም ምሳሌ 29:25ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ሰውን ሳይሆን አምላክን ላለማሳዘን እንድንፈራ የሚያደርጉንን አምስት ምክንያቶች ይዘረዝራል።” ገጽ 12 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
ንቁ! መጋቢት 2009
“ሁላችንም ጥሩ ጓደኞች እንዲኖሩን እንፈልጋለን። ጓደኛህ ምን ዓይነት ባሕርይ እንዲኖረው ትፈልጋለህ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጓደኛ ምን እንደሚል ልብ በል። [ምሳሌ 17:17ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ጥሩ ጓደኞች ለመምረጥ እንዲሁም እኛ ራሳችን ለሌሎች ጥሩ ጓደኞች ለመሆን የሚያስችሉንን ሐሳቦች ይዟል።” ገጽ 18 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“ኢየሱስ እዚህ ጥቅስ ላይ የተናገረውን ሐሳብ እንዴት እንደሚረዱት ቢገልጹልኝ ደስ ይለኛል። [ዮሐንስ 3:3ን አንብብ።] ዳግመኛ መወለድ ሲባል ምን ማለት ይመስሎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ስለዚህ ጉዳይ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘታችን የአሁኑን ሕይወታችንንም ሆነ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ያለንን አመለካከት የሚነካው እንዴት እንደሆነ ይህ መጽሔት ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ 2009
“በርካታ ልጆች በትምህርት ቤት ውጥረት ያጋጥማቸዋል። አሁን ያለው ሁኔታ ወላጆቻቸው ተማሪዎች ከነበሩበት ጊዜ የተለወጠ ይመስሎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ከመጠን ያለፈ ውጥረት አደገኛ ሊሆን ይችላል። [መክብብ 7:7ሀን ከ1954 ትርጉም ላይ አንብብ።] ይህ መጽሔት ልጆች የሚያጋጥማቸውን ውጥረት እንዲቋቋሙ ለመርዳት አዋቂዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ ያብራራል።”