መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ
“ሰዎች ኢየሱስን በተመለከተ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ የተለያዩ አመለካከቶች አሏቸው። እርስዎስ ኢየሱስን የሚመለከቱት እንደ አምላክ ልጅ አድርገው ነው ወይስ ጥሩ ሰው እንደሆነ ብቻ አድርገው?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም በገጽ 16 እና 17 ላይ ጎላ ብለው ከተጻፉት ጥያቄዎች መካከል አንዱን ከመረጥክ በኋላ ከታች ያለውን ሐሳብና አንዱን ጥቅስ አብራችሁ አንብቡ። መጽሔቶቹን አበርክትለትና በሌላው ጥያቄ መልስ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጋቢት 2011 ንቁ!
አንድ ወጣት ስታገኝ በገጽ 26 ላይ ያለውን ርዕስ አሳየው። የመጀመሪያውን ንዑስ ርዕስ በማሳየት እንዲህ በል፦ “እስቲ ለእነዚህ ጥያቄዎች እውነት ወይም ሐሰት የሚል መልስ ስጥ። [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም 2 ቆሮንቶስ 7:1ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ከማጨስ ጋር በተያያዘ ምን ማወቅ እንዳለብህና ማጨስ ማቆም የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ይናገራል።”
ሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ
“ብዙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ በጣም የተለያየ አመለካከት አላቸው። ይሁንና ስለ ኢየሱስ እውነቱን ማወቅ አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ኢየሱስ ከየት እንደመጣ፣ ሕይወቱ ምን ይመስል እንደነበረና ለምን እንደሞተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ያብራራል።”
ሚያዝያ 2011 ንቁ!
“የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት ሰዎች ከሚደርሱባቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉ እጅግ የከፋው ነው ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙዎች ይህን ምክር ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። [መዝሙር 55:22ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሸክማችንን በአምላክ ላይ መጣል የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚናገረውን ሐሳብ ጨምሮ ሐዘንን ለመቋቋም የሚረዱ ተግባራዊ ምክሮችን ይሰጣል።”