የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ጥምቀት በብዙ የክርስትና እምነቶች ዘንድ የተለመደ ሥነ ሥርዓት ነው። እርስዎስ ጥምቀት አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ጽሑፍ በዚህ ረገድ አንዳንድ ትኩረት የሚስቡ ነጥቦችን ይዟል።” የሚያዝያ 1ን መጠበቂያ ግንብ ለቤቱ ባለቤት ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ አብራችሁ ተመልከቱ፤ በተጨማሪም ቢያንስ አንድ ጥቅስ አንብቡ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ
“ሰዎች ስለ ኢየሱስ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኢየሱስ ተስፋ የተደረገበት መሲሕ እንደነበረ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲሁ ጥሩ ነገር ሠርቶ ያለፈ ሰው ብቻ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ የሚባል ሰው በምድር ላይ ኖሮ እንደማያውቅ የሚናገሩ ሰዎች አሉ። በዚህ ረገድ የእርስዎ አመለካከት ምንድን ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስለ ኢየሱስ ትክክለኛውን ነገር ማወቅ አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል። [ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሰዎች ኢየሱስን በተመለከተ ለሚያነሷቸው የተለመዱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።”
ሚያዝያ ንቁ!
“ወደ ቤታችሁ የመጣነው ለቤተሰቦች የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ለማካፈል ነው። በዛሬው ጊዜ ያሉ ቤተሰቦች የሚጋፈጧቸው ተፈታታኝ ሁኔታዎች በርካታ ናቸው ቢባሉ አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አብዛኞቹ ቤተሰቦች ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ምክር ያገኙት ከየት እንደሆነ እስቲ እንመልከት። [መዝሙር 119:105ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የእንጀራ ልጆች ያሏቸው ወላጆች የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በመከተል ያጋጠሟቸውን ለየት ያሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች በተሳካ መንገድ መወጣት የቻሉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”