የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ብዙዎቻችን ለችግሮቻችን መፍትሔ ማግኘት እንፈልጋለን። የሰው ልጆችን ችግሮች በሙሉ ሊያስወግድ የሚችለው ምን ዓይነት መንግሥት ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ አንድ መጽሔት ላሳይዎት።” የኅዳር 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም መጽሔቶቹን አበርክትለትና በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ
“እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት። አምላክን አንድ ጥያቄ መጠየቅ ቢችሉ ኖሮ ምን ብለው ይጠይቁት ነበር? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በቅንነት አምላክን መጠየቅ ተገቢ እንደሆነ ኢየሱስ ገልጿል። [ማቴዎስ 7:7ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ለሚከተሉት ሦስት ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ያብራራል።” ለምታነጋግረው ሰው በገጽ 3 መጨረሻ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች አሳየው።
ኅዳር ንቁ!
“ወደ ቤታችሁ የመጣነው ለቤተሰቦች የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ለማካፈል ነው። በነጠላ ወላጅ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች እየበዙ ነው። እነዚህ ቤተሰቦች ሁለት ወላጅ ካለበት ቤተሰብ የበለጠ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በርካታ ወላጆች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክር አግኝተዋል። [2 ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ነጠላ ወላጆች ያለባቸውን ከባድ ኃላፊነት እንዴት መወጣት እንደሚችሉ የሚገልጽ አንዳንድ ነጥቦችን ይዟል።”