የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“አንድ ጥያቄ ብጠይቅዎ ደስ ይለኛል፦ የአምላክ ስም ማነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ይህን ርዕስ ይመልከቱ።” የጥር 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በመጨረሻው ገጽ ላይ ያለውን ዓምድ አሳየው። ከዚያም በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ባለው ሐሳብ እና በዚያ ውስጥ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“ብዙ ሰዎች ስለ ዓለም መጨረሻ ሲናገሩ ይሰማል። የዓለም መጨረሻን መፍራት ያለብን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ አንድ ጥቅስ ላንብብልዎት። [1 ዮሐንስ 2:17ን አንብብ።] ይህ ጥቅስ እንደሚናገረው የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ። ይህ መጽሔት የዓለም መጨረሻን አስመልክቶ ብዙ ሰዎች ለሚያነሷቸው አራት ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ይዟል።”
ንቁ! ጥር
“ወደ ቤታችሁ የመጣነው ለቤተሰብ የሚጠቅሙ አንዳንድ ሐሳቦችን ለማካፈል ነው። [የሐዋርያት ሥራ 20:35ለን አንብብ።] ቤተሰቦች ኢየሱስ የተናገረውን ይህን ሐሳብ በሥራ ላይ ማዋላቸው አስፈላጊ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙዎች ስለራሳቸው ብቻ በሚያስቡበት በዚህ ዓለም ውስጥ ልጆችን ራስ ወዳድ እንዳይሆኑ አድርጎ ማሳደግ በጣም ተፈታታኝ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ይህ ርዕስ ወላጆች፣ ልጆቻቸው ጨዋ እንዲሆኑ መርዳት የሚችሉባቸውን አንዳንድ መንገዶች ይጠቁማል።”