የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ሰዎች የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ ከመሆኑም ሌላ አምላክን በተለያየ መንገድ ያመልካሉ። ስለዚህ ጉዳይ አምላክ ምን የሚሰማው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንዳለ ይመልከቱ።” ከዚያም የነሐሴ 1ን መጠበቂያ ግንብ ለቤቱ ባለቤት ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው የመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ አብራችሁ ተመልከቱ፤ በተጨማሪም ቢያንስ አንድ ጥቅስ አንብቡ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በሌላ ጊዜ ተገናኝታችሁ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ
“ልጆች ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ስለ አምላክ ቢማሩ ጥሩ ነው? ወይስ በዕድሜ ከፍ እስኪሉ ድረስ መጠበቅና የራሳቸውን ሃይማኖት እንዲመርጡ ማድረግ ይሻላል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ አባቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚናገረውን ሐሳብ ይመልከቱ። [ኤፌሶን 6:4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ አምላክ እንዴት ማስተማር እንደሚችሉ አንዳንድ ሐሳቦች ይሰጣል።”
ነሐሴ ንቁ!
“ይህን ጥቅስ በተመለከተ ምን ሐሳብ እንዳለዎት ብሰማ ደስ ይለኛል። [1 ሳሙኤል 16:23ን አንብብ።] ከዚህ ጥቅስ መመልከት እንደምንችለው ሙዚቃ ኃይል አለው። ታዲያ አንዳንድ ዘፈኖች መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድሩብን እንደሚችሉ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት በሙዚቃ ረገድ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ እንዴት ማድረግ እንደምንችልና ልጆቻችንም መራጭ እንዲሆኑ እንዴት እንደምንረዳቸው ያብራራል።”