የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰዎች ስለ መላእክት ለማወቅ ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል። መላእክት በእርግጥ አሉ ብለው ያምናሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ስለዚህ ጉዳይ ይህ መጽሔት ምን እንደሚል ልብ ይበሉ።” የሐምሌ 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም መጽሔቶቹን አበርክትለትና በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ሐምሌ 1
መዝሙር 65:2ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “ብዙዎች እዚህ ላይ እንደተጠቀሰው አምላክ ጸሎትን እንደሚሰማ ስለሚያምኑ በየቀኑ ይጸልያሉ። አንዳንድ ሰዎች ግን ‘በእርግጥ አምላክ ካለ፣ በዓለም ላይ ይህ ሁሉ ችግር እንዴት ሊኖር ቻለ?’ ብለው ይጠይቃሉ። እርስዎ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? ጸሎታችንን የሚሰማ አምላክ አለ ብለው ያምናሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት ‘ጸሎትን የሚሰማው አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?’ ለሚለው ጥያቄ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መልስ ይሰጣል።
ሐምሌ
“አቅም ቢኖርዎት ኖሮ በዓለም ላይ ካሉት ችግሮች መካከል የትኛውን ያስወግዱ ነበር? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጆች አቅም ውስን የሆነበትን ምክንያት ይገልጻል። [ኤርምያስ 10:23ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ ወደፊት ስለሚለውጣቸው ነገሮች ያብራራል።”