የናሙና አቀራረቦች
በግንቦት ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“‘አምላክ ክፋትና መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህን በተመለከተ አንድ ግሩም ሐሳብ ባካፍልዎት ደስ ይለኛል።” በግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ እትም ገጽ 16 ላይ ከሚገኘው የመጀመሪያ ንዑስ ርዕስ በታች ያለውን ሐሳብና አንዱን ጥቅስ አብራችሁ አንብቡ። መጽሔቶቹን አበርክትለትና በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ
መዝሙር 37:10, 11ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “በቅርቡ ይህ ተስፋ ፍጻሜውን ሲያገኝ መመልከት የምንችል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት፣ አሁን ያነበብነው ተስፋ በቅርቡ እንደሚፈጸም የሚጠቁሙትንና በአሁኑ ወቅት እየተፈጸሙ ያሉትን ስድስት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ያብራራል።”
ግንቦት 2011 ንቁ!
“የሰው ልጆች በዝግመተ ለውጥ አማካኝነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ እንስሳት እንደሆኑ አንዳንዶች ይናገራሉ። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም መዝሙር 139:14ን አንብብ።] እርግጥ ነው፣ መዝሙራዊው የሰው አካል ስላሉት አስደናቂ ነገሮች ያለው እውቀት ውስን ነበር። ይህ መጽሔት ስለ ሰው ልጅ አካል የደረስንበትን እውቀትና ከእንሰሳት የሚለየን ምን እንደሆነ ያብራራል።”