የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ሃይማኖት በሰዎች መካከል ፍቅርና ሰላም እንዳሰፈነ ይሰማዎታል? ወይስ ጥላቻና ዓመጽ እንዳስፋፋ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በዚህ ረገድ አንድ ትኩረት የሚስብ ሐሳብ ባሳይዎት ደስ ይለኛል።” የግንቦት 1ን መጠበቂያ ግንብ ለቤቱ ባለቤት ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ አብራችሁ ተመልከቱ፤ በተጨማሪም ቢያንስ አንድ ጥቅስ አንብቡ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ግንቦት 1
“ብዙ ሰዎች ሃይማኖት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ቢገባ ጥሩ እንደሆነ ይሰማቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ ሃይማኖት ከፖለቲካ ነፃ መሆን እንዳለበት ያምናሉ። በዚህ ረገድ የእርስዎ አመለካከት ምንድን ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ፣ ሰዎች በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ እንዲገባ ለማድረግ በሞከሩበት ወቅት ምን እንዳደረገ እስቲ እንመልከት። [ዮሐንስ 6:15ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ኢየሱስ እንዲህ ያደረገው ለምን እንደሆነ እንዲሁም ክርስቲያኖች ለሚኖሩበት ማኅበረሰብ ጠቃሚ ድርሻ ማበርከት የሚችሉበትን ከሁሉ የተሻለውን መንገድ ያብራራል።”
ግንቦት
“ሁሉም ሰው ለማለት ይቻላል በሕይወቱ ውስጥ ቢያንስ በአንድ ወቅት የፍትሕ መጓደል ደርሶበታል። የፍትሕ መዛባት መፍትሔ የሚኖረው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ የፍትሕ መዛባትን ስለሚያስወግድ አንድ መሪ የተናገረውን ትንቢት እስቲ እንመልከት። [መዝሙር 72:11-14ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ፍትሕ የሚሰፍንበት ጊዜ እንደሚመጣ ስለሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ያብራራል።”