የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/12 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • የናሙና አቀራረቦች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የናሙና አቀራረቦች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 5/12 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ

ዘፀአት 6:3⁠ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “በዚህ ጥቅስ መሠረት አምላክ ስም አለው። የአምላክን ስም መጠቀማችን አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ላሳይዎት።” የሰኔ 1⁠ን መጠበቂያ ግንብ ለቤቱ ባለቤት ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ አብራችሁ ተመልከቱ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።

ሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ

“ትኩረት ሊሰጠው ስለሚገባው ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት? [ገጽ 3 ላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች አሳየው።] እርስዎ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለዎትን አመለካከት የሚገልጸው ነጥብ የትኛው ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ ሲናገር ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [ሮም 15:4⁠ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስን ልዩ መጽሐፍ የሚያደርጉትን አምስት ምክንያቶች እንዲሁም ይህ መጽሐፍ የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”

ሰኔ ንቁ!

“በየዓመቱ፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የተበከለ ምግብ በመብላታቸው ምክንያት ይታመማሉ። በአካባቢያችን ያለው ምግብ ንጽሕናውን የጠበቀ እንደሆነ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት ቤተሰባችንን ከምግብ ወለድ በሽታዎች መጠበቅ የምንችልበትን አራት መንገዶች ያብራራል። በተጨማሪም በቅርቡ ጤናማ ምግብ የሚትረፈረፍበት ጊዜ እንደሚመጣ ስለሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ማብራሪያ ይሰጣል።” መዝሙር 104:14, 15⁠ን አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ