የናሙና አቀራረቦች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ማናችንም ብንሆን በሞት ያጣነው የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ ይኖረናል። ታዲያ እነዚህን ሰዎች እንደገና አገኛቸዋለሁ የሚል ተስፋ አለዎት? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ይህን የሚያጽናና ሐሳብ ይመልከቱ።” በሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እትም ገጽ 16 ላይ ከሚገኘው የመጀመሪያ ንዑስ ርዕስ በታች ያለውን ሐሳብና አንዱን ጥቅስ ካነበብክ በኋላ ተወያዩበት። መጽሔቶቹን አበርክትለትና በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“ብዙዎቻችን የሚያስፈልጉንን ነገሮች ማሟላት የምንችለው በብዙ ውጣ ውረድ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን እንኳ ማግኘት አይችሉም። ይሁንና ድህነት ፈጽሞ የማይኖርበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም መዝሙር 9:18ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የድህነት መንስኤ ምን እንደሆነና ድህነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዴት እንደሚወገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ሐሳብ ያብራራል።”
ንቁ! ሰኔ 2011
“ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ ችግር ሆኗል። የዚህ ችግር መንስኤ ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙት እነዚህ ቃላት ተስፋ ያዘሉ ናቸው። [መዝሙር 72:7, 14ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ለሽብርተኝነት መንስኤ የሆኑ አንዳንድ ምክንያቶችንና መጽሐፍ ቅዱስ ሽብርተኝነት እንዴትና መቼ እንደሚወገድ የሚናገረውን ሐሳብ ያብራራል።”