የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“በዛሬው ጊዜ አብዛኞቹ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ሲያስቡ ወደ አእምሯቸው የሚመጣው በግርግም ውስጥ የተኛ ሕፃን ወይም ደግሞ በመከራ እንጨት ላይ የተሰቀለ ሰው ነው። እርስዎ ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ ምን እያደረገ ያለ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ አንድ መጽሔት ላሳይዎት።” የነሐሴ 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም መጽሔቶቹን አበርክትለትና በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ብዙ ሰዎች በተአምራት ያምናሉ። ሌሎች ግን ተአምራት መፈጸም መቻላቸውን ይጠራጠራሉ። እርስዎ ተአምራት ሊፈጸሙ የሚችሉ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ወደፊት የሚፈጸም አንድ ተአምር አለ፤ ብዙ ሰዎች በዚህ ተአምር ላይ ያላቸው እምነት ብሩሕ ተስፋ እንዲኖራቸው አድርጓል። [ከገጽ 9-10 ላይ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል አንዱን አንብብ።] ይህ መጽሔት በተአምር የማያምኑ ሰዎች ለሚያነሷቸው ሦስት የተቃውሞ ሐሳቦች መልስ ይሰጣል።”
ነሐሴ ንቁ!
“በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች፣ በተለይ ከመሸ በኋላ ብቻቸውን ከቤት መውጣት ያስፈራቸዋል። በዓለማችን የሚታዩትን የዓመፅ ድርጊቶች ለመቀነስ ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች ያሉ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ይበልጥ ሰላማዊ ለመሆን ሁላችንም ማድረግ የምንችላቸውን አንዳንድ ነገሮች ይጠቁመናል። በተጨማሪም በመዝሙር 72:7 ላይ የሚገኘው አስደሳች ትንቢት እንዴት እንደሚፈጸም ያብራራል።” ጥቅሱን አንብብ።