የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“አምላክን ለመታዘዝ ጥረት የሚያደርጉ ሰዎች ደስተኞች እንደሆኑ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እዚህ ርዕስ ላይ ጥሩ ሐሳቦችን ያገኛሉ።” ከዚያም የኅዳር 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 16 እና 17 ላይ ካሉት ንዑስ ርዕሶች መካከል አንዱን መርጣችሁ ተወያዩበት። በተጨማሪም በንዑስ ርዕሱ ውስጥ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አንብቡ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ ከቀሪዎቹ ጥያቄዎች መካከል በአንዱ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ
“አንዳንዶች ከፆታ ሥነ ምግባር ጋር በተያያዘ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ሐሳብ ጊዜ ያለፈበትና የማያፈናፍን እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚሰጠው መመሪያ ጋር ይስማማሉ። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:16 ላይ የሚገኘው ሐሳብ የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች ምንጭ ማን እንደሆነ ይናገራል። [ጥቅሱን አንብብ።] ስለ ፆታ ግንኙነት ለሚነሱ አሥር ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው መልስ እዚህ መጽሔት ላይ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶችን መከተል የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ኅዳር ንቁ!
“በዙሪያችን ያለውን አጽናፈ ዓለም ቆም ብለን ስንመለከት ምን ዓይነት መደምደሚያ ላይ የምንደርስ ይመስልዎታል? ፈጣሪ መኖሩን ወይስ ሁሉም ነገር የመጣው በአጋጣሚ መሆኑን? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ አጽናፈ ዓለምን ከተመለከተ በኋላ የደረሰበትን መደምደሚያ አብረን እንመልከት። [ሮም 1:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የሳይንስ ሊቃውንት ስለ ሰው ልጆች ሴል የደረሱበትን ነገርና ይህ ደግሞ በአመለካከታችን ላይ የሚያመጣውን ለውጥ ያብራራል።”