ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ኅዳር እና ታኅሣሥ፦ ከሚከተሉት ትራክቶች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል! ወይም እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? ግለሰቡ ፍላጎት ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አሊያም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ በተባለው ብሮሹር ተጠቅማችሁ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንደሚችል ልታሳዩት ትችላላችሁ። ጥር፦ ከሚከተሉት ባለ32 ገጽ ብሮሹሮች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት ወይም የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ መጋዘናችን ውስጥ አዲስ የገቡ፦ እንግሊዝኛ፦ በኤርምያስ በኩል የተላለፈልን የአምላክ ቃል በሲዲ።