መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“ሁሉም ሰው በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ቢመራ ዓለማችን የተሻለች ቦታ የምትሆን አይመስልዎትም? [ሮም 12:18ን አንብብ። ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ታዲያ አምላክ በጥንት ጊዜ ለነበሩት ሕዝቦቹ እንዲዋጉ የፈቀደላቸው ለምንድን ነው? ብለው ይጠይቁ ይሆናል። ይህ ርዕሰ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውን ግልጽ መልስ ይዟል።” ገጽ 13 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ጥር 2010
የሐዋርያት ሥራ 17:31ን አንብብ። ከዚያም “የፍርድ ቀን የሚለው ሐሳብ ለብዙዎች አስፈሪ ነው። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በፍርድ ቀን በምድር ላይ ብዙ በረከት እንደሚትረፈረፍ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ ርዕስ ስለዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይሰጣል።” ገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“በርካታ ሰዎች ‘ስንሞት ወደ ሰማይ እንሄዳለን’ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። እርስዎስ ተስፋ የሚያደርጉት ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አብዛኞቹ ጥሩ ሰዎች ምን ተስፋ እንዳላቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ልብ ይበሉ። [መዝሙር 37:29ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን እንደሆኑና እዚያ የሚሄዱት ለምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ሐሳብ ያብራራል።”
ንቁ! የካቲት 2010
“በዛሬው ጊዜ ፍቺ በጣም የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል። አብዛኞቹ ባለትዳሮች ለመፋታት ከመወሰናቸው በፊት ከፍቺ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ቆም ብለው የሚያስቡበት ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ምሳሌ 14:15ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ባለትዳሮች ለመፋታት ሲያስቡ ግምት ውስጥ ሊያስገቧቸው የሚገቡ አራት ነጥቦችን ይዟል።”