ነሐሴ 8 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 44 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 15 አን. 20-25 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 92-101 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 94:1-23 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የአምላክ መንግሥት ለመላው የሰው ልጅ የተትረፈረፈ ምግብ ያቀርባል እንዲሁም ሕመምን ያስወግዳል—rs ገጽ 229 አን. 6-8 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ሀብት ያለው የማታለል ኃይል እንዳያሸንፈን መጠንቀቅ—ማቴ. 13:22 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ለቤቱ ባለቤት አሳቢነት አሳዩ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 186-187 ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። የቀረቡትን ነጥቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመር ረገድ የተገኙ ተሞክሮዎች። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመር ረገድ የተደረገውን ዝግጅት በመደገፉ ጉባኤውን አመስግን። አድማጮች ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ግሩም ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲቀርቡ ማድረግ ትችላለህ።
10 ደቂቃ፦ “የአምላክ ስም ይቀደስ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የወረዳ ስብሰባው ቀን የሚታወቅ ከሆነ ተናገር።
መዝሙር 2 እና ጸሎት