ጥቅምት 3 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 18 አን. 1-9 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 1-6 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ምሳሌ 6:1-19 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ሮም 8:26, 27 አምላክ እንደሚወደን የሚያረጋግጥልን እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንግሥት መግዛት እንዲጀምር በመጀመሪያ ዓለም ወደ ክርስትና መለወጥ ይኖርበታል?—rs ገጽ 233 አን. 1-2 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ ሉቃስ 5:12, 13ን እና ሉቃስ 8:43-48ን አንብቡ። ከዚያም እነዚህ ጥቅሶች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ እንዴት እንደሚረዱን ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በአገልግሎት ላይ መልካም ምግባር አሳዩ። (2 ቆሮ. 6:3) በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ፦ (1) በአገልግሎት ላይ በምንሆንበት ጊዜ መልካም ምግባር ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው? (2) በሚከተሉት ጊዜያት ይኸውም (ሀ) አብረን ከተመደብናቸው አስፋፊዎች ጋር ወደ አገልግሎት ክልሉ ስንደርስ፣ (ለ) ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ስንሄድ፣ (ሐ) ቤቱ በር ላይ ስንቆም፣ (መ) የአገልግሎት ጓደኛችን ሲመሠክር፣ (ሠ) የቤቱ ባለቤት ሲናገር፣ (ረ) የቤቱ ባለቤት ሥራ ላይ ከሆነ ወይም የአየሩ ጠባይ መጥፎ ሲሆን እንዲሁም (ሰ) የቤቱ ባለቤት ተሳዳቢ ሲሆን መልካም ምግባር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
መዝሙር 16 እና ጸሎት