የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 29, 2012 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. ሕዝቅኤል በራእይ ያየው መሠዊያ ምን ያመለክታል? (ሕዝ. 43:13-20) [መስ. 10, w07 8/1 ገጽ 10 አን. 4]
2. ሕዝቅኤል ስለ ወንዙ በተመለከተው ራእይ ላይ ውኃው ምን ያመለክታል? (ሕዝ. 47:1-5) [መስ. 17, w07 8/1 ገጽ 11 አን. 2]
3. “በልቡ አሰበ” የሚለው ሐረግ ዳንኤል በልጅነቱ ስላገኘው መንፈሳዊ ሥልጠና ምን ይጠቁማል? (ዳን. 1:8 የ1954 ትርጉም) [መስ. 24, dp ገጽ 33-34 አን. 7-9፤ ገጽ 36 አን. 16]
4. ናቡከደነፆር በሕልሙ ያየው ረጅም ዛፍ ምን ያመለክታል? (ዳን. 4:10, 11, 20-22) [ጥቅ. 1, w07 9/1 ገጽ 18 አን. 4]
5. ከጸሎት ጋር በተያያዘ ከዳንኤል 9:17-19 ምን ትምህርት እናገኛለን? [ጥቅ. 8, w07 9/1 ገጽ 20 አን. 5-6]
6. ሰባዎቹ የዓመታት ሳምንታት እስኪያበቁ ማለትም እስከ 36 ዓ.ም. ድረስ ‘ከብዙ ሰዎች ጋር የጸናው ቃል ኪዳን’ የትኛው ነው? (ዳን. 9:27) [ጥቅ. 8, w07 9/1 ገጽ 20 አን. 4]
7. አንድ መልአክ “የፋርስ መንግሥት አለቃ” እንደተቋቋመው ለዳንኤል መናገሩ ምን እንድንገነዘብ ያደርገናል? (ዳን. 10:13) [ጥቅ. 15, w11 9/1 ገጽ 8 አን. 1-2]
8. ከዳንኤል 11:20 ጋር በተያያዘ መሲሑን አስመልክቶ የተነገረው የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቷል? [ጥቅ. 15, dp ገጽ 232-233 አን. 5-6]
9. በሆሴዕ 4:11 (የ1954 ትርጉም) መሠረት ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት ከሚያስከትላቸው አደጋዎች አንዱ ምንድን ነው? [ጥቅ. 22, w10 1/1 ገጽ 4-5]
10. ከሆሴዕ 6:6 ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? [ጥቅ. 22, w07 9/15 ገጽ 16 አን. 8፤ w05 11/15 ገጽ 24 አን. 11-12]