ጥቅምት 29 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 13 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
w09 2/15 ገጽ 10-11 ከአን. 1-7 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሆሴዕ 8-14 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ “ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ቡድናችሁ ጥቅም ማግኘት የምትችሉት እንዴት ነው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ገጽ 6 ላይ ባለው ሣጥን ላይ ስትወያዩ በቤቱ የስምሪት ስብሰባ ለሚደረግ አንድ አስፋፊ አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። በየሳምንቱ በቤቱ ውስጥ ለሚከናወነው የስምሪት ስብሰባ ምን ዝግጅት ያደርጋል? እንዲህ ያለ ስብሰባ በቤቱ መከናወኑ ትልቅ መብት እንደሆነ የሚሰማው ለምንድን ነው?
15 ደቂቃ፦ “ጥናት ለማግኘት የሚያስችሉ አምስት መንገዶች።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 6 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ እድገት የሚያደርግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይመሩ የነበሩ አስፋፊዎች ስላገኙት ደስታ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 31 እና ጸሎት