መዝሙር 31
የይሖዋ ምሥክሮች ነን!
በወረቀት የሚታተመው
1. ሰዎች ከድንጋይ ከ’ንጨት፣ ይሠራሉ አማልክት።
ሁሉን ቻይ አምላክን፣ አላወቁትም።
ጣዖታት ናቸው ከንቱ፤
መተንበይ የማይችሉ።
አምላክነታቸው ውሸት ነው፤
ምንም ማስረጃ የሌለው።
(አዝማች)
ያምላክ ትንቢት እውነት ነው፤
ይፈጸማል በጊዜው።
የይሖዋ ምሥክሮች ነን፤
እንመሥክር ተማምነን።
2. ስሙን እናውጃለን፤ ዝናውን ’ናወራለን።
የአምላክን መንግሥት እንሰብካለን።
ሰዎች እውነትን አውቀው፣
ነፃ ይውጡ ተምረው።
እነሱም እድገት ካደረጉ፣
አምላክን ያወድሳሉ።
(አዝማች)
ያምላክ ትንቢት እውነት ነው፤
ይፈጸማል በጊዜው።
የይሖዋ ምሥክሮች ነን፤
እንመሥክር ተማምነን።
3. ምሥክርነታችን ስሙን ያስከብረዋል።
ያምላክን ጠላቶች ያስጠነቅቃል።
ንስሐ ከገቡ ግን
ያገኛሉ ምሕረቱን።
ደስታ፣ ሰላም ይኖራቸዋል፤
ተስፋቸው ይለመልማል።
(አዝማች)
ያምላክ ትንቢት እውነት ነው፤
ይፈጸማል በጊዜው።
የይሖዋ ምሥክሮች ነን፤
እንመሥክር ተማምነን።
(በተጨማሪም ኢሳ. 37:19፤ 55:11ን እና ሕዝ. 3:19ን ተመልከት።)